Tefa Maninete

ቃል በላሁ ዘንድሮ ስሜቴም ተጎዳ
ምገባበት ጠፋኝ መንፈሴን ብረዳ
እንደ ደራሽ ውሀ ምስቅልቅል ህይወቴ
የያዝኩትን ስጥል ጠፋ ማንነቴ
ስንት አዋቂ አባቶች በገነቧት ሀገር
ማንነቴን ጥዬ ባህር ማዶ ሳማትር
እንደዛሬ ሳልሆን ስልጣኔ እያልኩኝ
ያኔማ የኔታ ነበር ያስተማሩኝ
ባላየው እኔስ አስተውዬ ፍሬውን ከገከባ
ትንሽ አውቀቴ ዛሬ አጠፋኝ በቃ ይዞኝ ገደል ገባ
ኋላ ቀር እያልኩኝ ሳጣጥል ስንቀው የበፊቱን
የህይውቴን መሰረት ምሶሶዬን አጣሁት ድጋፉን
ባዛውንቶች ራስ በጠሊቅ እውቀታቸው
መንገድ በሚያቀና ምክር ግሳጼያቸው
ስንት ለፍተው ደክመው ሀገር ሰጥተውኛል
እኔ ግን የሌላ ሀገር ጠረን ይስበኛል
ቋንቋዬም ተዛባ ጉራማይሌ ሆነ
ይሀው ጉብዝናዬ በከንቱ ባከነ
እስክስታዬን ትቼ በጥሱ ታጥኜ
ቅጠል እበላለሁ አልኖርም መጥኜ
ባላየው እኔስ አስተውዬ ፍሬውን ከገከባ
ትንሽ አውቀቴ ዛሬ አጠፋኝ በቃ ይዞኝ ገደል ገባ
ኋላ ቀር እያልኩኝ ሳጣጥል ስንቀው የበፊቱን
የህይውቴን መሰረት ምሶሶዬን አጣሁት ድጋፉን
የህይወት ዙረቱ የሰው መጨረሻ
ለስሙ ማስታወሻ ትቶ ማለፉን
ባህሌን ታሪኬን ካላልኩኝ በስተቅር
ሌላውማ የ ሰው ሰው ሆኖ መች ሊቀር
ዛሬ ቆመው ሲያዩት ባህር ማዶ ያስቀናል
ያ የሩቅ ሰው ግን ስንት ለፍቶበታል
ስለራሴ ሳላውቅ የሰው ፈትፍቻለው
ማነህ አንት ቢሉኝ ቆይ እኔ ምን ልል ነው
ባላየው እኔስ አስተውዬ ፍሬውን ከገከባ
ትንሽ አውቀቴ ዛሬ አጠፋኝ በቃ ይዞኝ ገደል ገባ
ኋላ ቀር እያልኩኝ ሳጣጥል ስንቀው የበፊቱን
የህይውቴን መሰረት ምሶሶዬን አጣሁት ድጋፉን
ባላየው እኔስ አስተውዬ ፍሬውን ከገከባ
ትንሽ አውቀቴ ዛሬ አጠፋኝ በቃ ይዞኝ ገደል ገባ
ኋላ ቀር እያልኩኝ ሳጣጥል ስንቀው የበፊቱን
የህይውቴን መሰረት ምሶሶዬን አጣሁት ድጋፉን



Credits
Writer(s): Getaneh Bitew
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link