Armash

አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ
ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ
እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ
ሀገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ
ቀን እየሄደ ቀን መጣ
ልቤ ከሀሳብ ሳይወጣ
መጥታ ታብሰው እንባዬን
ሀገሬን ጥሯት አርማዬን
መቼም ከዚህ ምድር ላይ ሄዶ ነው ሁሉም ቀሪ
አገር ናት ቋሚ ሰንደቅ ለዘላለም ኗሪ
ትላንትም እንደ ጀምበር እያዩት ካይን ይርቃል
ኢትዮጵያ እንድትመጪ ስንት ቀን ይበቃል
እኔማ ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ
ግን ባባሁ ናፈኩሽ እና ዕምባ ቀደመኝ
እኔማ አለሁ እስካሁን ተስፋ ሰንቄ
በወንዜ ባገሬ እያለሁ አገር ናፍቄ
ወጥተሽ በምሥራቅ አንቺ ያለም ጀምበር
አንድ አርጊንና ጠላትሽ ይፈር
የቦረኩበት በልጅነቴ
የያኔው መልክሽ ብቅ ሲል ፊቴ
እየመለሰኝ ወደ ትላንቱ
ናፍቆኝ በብርቱ ትዝ አለኝ የጥንቱ
እ... እ... እ...
አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ
ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ
እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ
ሀገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ
አገር ለክብሩ ሲጣራ
ከፍ ያደረግነው ባንዲራ
ዘመም ሳይል ቀን ጎሎ
ባክሽ ኢትዮጵያ ነይ ቶሎ
ብዙነሽ አንቺ አገሬ የሞላሽ ታምራት
ምኩራብሽ የተፈራ የነጻነት ቤት
የአርበኞች የድል ችቦ ለትውልድ እንዳበራ
መኖር ላገር ሲሆን ሞትም አያስፈራ
እኔማ ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ
ግን ባባሁ ናፈኩሽ እና ዕምባ ቀደመኝ
እኔማ አለሁ እስካሁን ተስፋ ሰንቄ
በወንዜ ባገሬ እያለሁ አገር ናፍቄ
ዓመት አውዳመት ድገመን ሲሉ
ልጆች በቀዬው ችቦ እያበሩ
መስቀል ፋሲካው ዒድ እንቁጣጣሽ
አውዳመት አይሆን አንቺ ካልመጣሽ
ዘመን አድሰሽ በፍቅር ቀለም
ብቅ በይ ኢትዮጵያ ሁኚና መስከረም
ሆነሽ መስከረም (አስዮ)
ብቅ በይና (ቤሌማ)
እንበል አሲዮ (አስዮ)
ናና ቤሌማ (ቤሌማ)
ብቅ በይና (አስዮ)
ሆነሽ ሙሽራ (ቤሌማ)
ይብቃን ስደቱ (አስዮ)
ስቃይ መከራ (ቤሌማ)
ቤሌም ቤሌማ (አስዮ)
ናና ቤሌማ (ቤሌማ)
ዘር ያበቀለው (አስዮ)
ታጭዷል መከራው (ቤሌማ)
የኢትዮጵያዊነት (አስዮ)
አሁን ነው ተራው (ቤሌማ)
አስዮ አስዮ (አስዮ)
ና ና ቤሌማ (ቤሌማ)
ቤሌማ (አስዮ)
ና ና ቤሌማ (ቤሌማ)
ዘመን አድሰሽ (አስዮ)
በፍቅር ቀለም (ቤሌማ)
ብቅ በይ ኢትዮጵያ (አስዮ)
ሆነሽ መስከረም (ቤሌማ)
እኛስ ከመንገድ ላይ ጠፍተን መች አወቅነው
ብንሄድ ብንሄድ አንደርስም ገና ነው
በመባረኪያችን ከመንገድ ላይ ዝለን
አይበቃም ወይ ማሳል በዘር ጉንፋን ታመን
በዘር ጉንፋን ታመን
ቀን አለ በሉ (አለ ገና)
ቀን አለ ገና (አለ ገና)
አለ በሉ (አለ ገና)
ቀን አለ ገና (አለ ገና)
ለኢትዮጵያዊነት ቀን አለው ገና
ስምሽን በክፉ ያነሳሽ ጠፍቶ
አርማሽ ከፍ ሲል ሰማይ ላይ ወጥቶ
እኛ ልጆችሽ ልናይ ቆመናል
አንድ ቀን መጥቶ አንድ ያደርገናል
ቀን አለ በሉ (አለ ገና)
ቀን አለው ገና (አለ ገና)
ቀን አለ በሉ
ቀን አለው ገና
ስንቱ ተሰደደ ይብቃን ሐዘን ለቅሶ
አንድ ሆነሽ ኢትዮጵያ ባየን ፍቅር ነግሦ
ዘር ያበቀለው ታጭዷል መከራው
የኢትዮጵያዊነት አሁን ነው ተራው
ቀና በል አሁን (ቀና በል)
ቀና በል ቀና (ቀና በል)
ቀና በል አሁን (ቀና በል)
ቀና በል ቀና (ቀና በል)
የጀግኖቹ ልጅ (ቀና በል)
አንተ ነህና (ቀና በል)
ካገር ወዲያ ሞት (ቀና በል)
ሞት የለምና (ቀና በል)
ዝም ያለ መስሎ ኢትዮጵያዊነት
ማንም አይገታው የተነሳ 'ለት
ቀና በል አሁን (ቀና በል)
ቀና በል ቀና (ቀና በል)
ጥንት አባቶችህ ያቆዩትን
ከፍ አርገህ ይዘህ ባንዲራህን
ቀና በል አሁን (ቀና በል)
ቀና በል ቀና (ቀና በል)
(ቀና በል)
(ቀና በል)
(ቀና በል)
(ቀና በል)
(ቀና በል)
(ቀና በል)
(ቀና በል)



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Theodros Kassahun
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link