Enjori

አንቺ የእንጆሪ ፍሬ መዓዛሽ እያማረኝ
በሳማ በቆንጥር በአጋም በጋሬጣ
በእሾህ ተከበሻል በየት በኩል ልምጣ
የወንዙ ዳር መውጫው አዳልጦ እየጣለኝ
የጭቃ እሾሁ ነው ይበልጥ ያስቸገረኝ
የጭቃ እሾሁ ነው ይበልጥ ያስቸገረኝ
አንቺ የእንጆሪ ፍሬ መዓዛሽ እያማረኝ
ከእሾህ ሐረግ በቅለሽ መውጫው አስቸገረኝ
እንዴት ያስደንቃል ውበት ጥፍጥናሽ
እሾህ ከበዛበት ምነው መብቀልሽ
ነብር አንበሳ ሞልቶ በጫካሽ በወንዙ
እባብ ነው ያስፈራኝ ባለ ትንፋሽ መርዙ
ከዘንዶው ከአዞውም ድንገት ከሚውጠው
እስስቷን ሳያት ነው የምደነግጠው
እንዲህ ተጨንቄ ላገኝሽ ናፍቄ
አንቺ እየለመለምሽ እኔ እንዲህ ደርቄ
ያንቺ ቁመት ሲያድግ የኔው እያጠረ
አንጋጦ ማየቱ ልምዴ ሆኖ ቀረ
አንጋጦ ማየቱ ልምዴ ሆኖ ቀረ
አንቺ የእንጆሪ ፍሬ መዓዛሽ እያማረኝ
ከእሾህ ሐረግ በቅለሽ መውጫው አስቸገረኝ
እንዴት ያስደንቃል ውበት ጥፍጥናሽ
እሾህ ከበዛበት ምነው መብቀልሽ
ከትልቁ ዛፍ ላይ ወጥተሽ ተጠምጥመሽ
ልመገብ አልቻልኩም ከጣፋጩ ፍሬሽ
ዋርካው ተገን ሆኖ ለሐሩሩ ጥላ
ሲያዩት ያስጎመጃል የፍሬሽ ዘለላ
እንዲህ ተጨንቄ ላገኝሽ ናፍቄ
አንቺ እየለመለምሽ እኔ እንዲህ ደርቄ
ያንቺ ቁመት ሲያድግ የኔው እያጠረ
አንጋጦ ማየቱ ልምዴ ሆኖ ቀረ
አዎ
አንጋጦ ማየቱ ልምዴ ሆኖ ቀረ
እንዲህ ተጨንቄ ላገኝሽ ናፍቄ
አንቺ እየለመለምሽ እኔ እንዲህ ደርቄ
ያንቺ ቁመት ሲያድግ የኔው እያጠረ
አንጋጦ ማየቱ ልምዴ ሆኖ ቀረ
ኡኡ
አንጋጦ ማየቱ ልምዴ ሆኖ ቀረ



Credits
Writer(s): Unknown Unknown, Samuel Alemu
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link