Abaree

መች ይጠፋል በደግ ቀን አባሪ
መች ይጠፋል በብራ ቀን አባሪ
ስያሜው ሚገባው እውነተኛ አፍቃሪ
ያንቺ አይነት ሲሆን ነው በክፉ ተጠሪ (የኔ)
መች ይጠፋል በደግ ቀን አባሪ
መች ይጠፋል በብራ ቀን አባሪ
ስያሜው ሚገባው እውነተኛ አፍቃሪ
ያንቺ አይነት ሲሆን ነው በክፉ ተጠሪ (የኔ)

አለው አለው ሚል ሁላ ስትፈልገው የለም
ሰው ባሻህም ጊዜ ቀድሞ አልተገኘም
በቃ ቁረጥልኝ ሁሉን አትመን ብዬ
ልቤን እንዳልሞግት ረታሽኝ አንቺዬ

ባንቺ የተማርኩት እውነት
ሰው መውደድ ንፁህ ማንነት
ደሞ ቅን ልብሽ የፍቅር ስጦታ
ማረከኝ እንዳምንሽ
ባንቺ የተማርኩት እውነት
ሰው መውደድ ንፁህ ማንነት
ደሞ ቅን ልብሽ የፍቅር ስጦታ
ማረከኝ እንዳምንሽ

መች ይጠፋል በደግ ቀን አባሪ
መች ይጠፋል በብራ ቀን አባሪ
ስያሜው ሚገባው እውነተኛ አፍቃሪ
ያንቺ አይነት ሲሆን ነው በክፉ ተጠሪ (የኔ)
መች ይጠፋል በደግ ቀን አባሪ
መች ይጠፋል በብራ ቀን አባሪ
ስያሜው ሚገባው እውነተኛ አፍቃሪ
ያንቺ አይነት ሲሆን ነው በክፉ ተጠሪ (የኔ)

ደግሜ ደግሜ ላሞካሽሽ ደግሜ
የእውነት መውደዴን ካንቺው ቀስሜ
ተጠቦ ተደንቆ መኖርን ባውቅም
ለክፉ ደራሽ ገጥሞኝ አያውቅም
ድሮም ድሮም ካንቺ በፊት
ይመስለኝ ነበር ሰው ሁሉ አንድ አይነት
ፍቅርን አውቆ ተቀይሮ
ልቤ በእጥፍ ወደደሽ ጨምሮ

ከሰማሁት ካየሁትም በላይ
ትለያለሽ ስል አልሆንም አባይ
አምና ሸለመችኝ ፍቅሯን
ታምና አሳየችኝ ልቧን
በከተማው ሺ ቆንጆ በሞላበት
ውበት አይን አዋጅ በሆነበት
ቢፈልግ ጠፍቷል ለኔ እንዳንቺ አይነት

ታማኝ ለካ ሰው አለ
ታማኝ ለካ ሰው አለ
ታማኝ ሰው አለ
ለካ ታማኝ ሰው አለ



Credits
Writer(s): Natnael Yimer
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link