Amelwa

እሷም እኔን መስላለች
እኔም እሷን እሷን
ፈቅዶ ነው ያላመደን
ፍቅር ያጣመረን
ፀባይዋን አመሏን
እንደ ህልሜ አድርጎት
የምኞቴን ሰው ባገኝ የልቤን ፍላጎት
ትሁን ትዘዝ ብዬ በላዬ እንዳልሾምኳት
እንደቃሏ ልገኝ በኪዳን አሰርኳት

ለእሷ ብቻ ቢያደላ እውነት አለው ልቤ
ሆና ተገኝታ ነው እንደ ሀሳቤ
ለወደደው ቢያደላ እውነት አለው ልቤ
ሆና ተገኝታ ነው እንደ ሀሳቤ

ወርቅ አመሏ ገዝቶኝ
ጥሩነቷ ማርኮኝ
እርም ሌላ ያስማለ
ለኔ የገባኝ ሀቅ አለ
ወርቅ አመሏ ገዝቶኝ
ጥሩነቷ ማርኮኝ
እርም ሌላ ያስማለ
ለኔ የገባኝ ሀቅ አለ

ግርማውን ሳቢ ውበቱን
ሸጋ አመል የሴትነቱን
በልኩ አጎናፅፋ ነገር ሁሉ ሲያምርላት
ለሀሰት ፅይፍ ማላሷ
ቅጥፈት አታውቅም እሷ
ደሞ በዚህ ዘመን
የለም ሲሉኝ ሚታመን
ከቀረብኩት ሁሉ እሷን ሚለያት
የባከነው ቀልቤ ሰከነላት
አንደበትስ ስሟን ቢያሞካሸው
ህይወቴ አምሮ ነው ህይወቴ አምሮ ነው

ለእሷ ብቻ ቢያደላ እውነት አለው ልቤ
ሆና ተገኝታ ነው እንደ ሀሳቤ
ለወደደው ቢያደላ እውነት አለው ልቤ
ሆና ተገኝታ ነው እንደ ሀሳቤ

ወርቅ አመሏ ገዝቶኝ
ጥሩነቷ ማርኮኝ
እርም ሌላ ያስማለ
ለኔ የገባኝ ሀቅ አለ
ወርቅ አመሏ ገዝቶኝ
ጥሩነቷ ማርኮኝ
እርም ሌላ ያስማለ
ለኔ የገባኝ ሀቅ አለ

(ሀቅ አለኝ እኔ)
(ሀቅ አለኝ እኔ)
(ሀቅ አለኝ እኔ)
(ሀቅ አለኝ እኔ)

ሀቅ አለኝ እኔ
ሀቅ አለኝ እኔ
ሀቅ አለኝ እኔ
ሀቅ አለኝ እኔ

አምኜ ብወዳት
ኮርቶ ነው ጎኔ
አምኖ ህይወትን

ሀቅ አለኝ እኔ
ሀቅ አለኝ እኔ
ሀቅ አለኝ እኔ
ሀቅ አለኝ እኔ



Credits
Writer(s): Natnael Yimer
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link