Senay

ውብ ልበ ተራራ የሰው ልክ እያሉ
ሲያደንቁሽ ሲያገኑሽ አንቺን ያዩሽ ሁሉ
ጉጉቴ እንዳልናረ እንዳልጨመረ
የልቤ ቢሞላ አፌ መሰከረ

የኔ ሴት ሰናይ ካሉኝም በላይ ሙሉ
የኔ ሴት ሰናይ አምሳለ እናት ጀግና ሙሉ
የኔ ሴት ሰናይ ካሉኝም በላይ ሙሉ
የኔ ሴት ሰናይ አምሳለ እናት ጀግና ኩሩ

የእውነት ደስተኛ ማነው እንደኔ የታደለው
እመር ድመቅ ተብሎ በፍቅር የተሸለመው
ካሉኝም ከሰማሁት ሁሉ በላይ
ሆነሽ በልጠሽ ተገኝተሽ ሀሳቤን ጣልኩ አንቺው ላይ
ሆነ ሰመረልኝ ሞላ የልቤ
ፍቅርን ስጋራ ካንቺው ቀርቤ
እንዲ ነኝ እንዲያ ነኝ ብለሽ ሳታወሪ
ተግባርሽ ይቀድማል ሆኖ ምስካሪ

የኔ ሴት ሰናይ ካሉኝም በላይ ሙሉ
የኔ ሴት ሰናይ አምሳለ እናት ጀግና ሙሉ
የኔ ሴት ሰናይ ካሉኝም በላይ ሙሉ
የኔ ሴት ሰናይ አምሳለ እናት ጀግና ኩሩ

ያሳደጏት ሚኮሩባት ያመኗት የሚመኩባት
የእናቷ ልጅ ሙሉ እንደ እናቴ ኩሩ
ያሳደጏት የሚመኩባት ያመኗት የማያፍሩባት
የእናቷ ልጅ ኩሩ እንደ እናቴ ሙሉ

ሰናይ ሰናይ ሰናይ

ያሳደጏት ሚኮሩባት ያመኗት የሚመኩባት
የእናቷ ልጅ ሙሉ እንደ እናቴ ኩሩ
ያሳደጏት ሚኮሩባት ያመኗት የሚመኩባት
የእናቷ ልጅ ኩሩ እንደ እናቴ ሙሉ



Credits
Writer(s): Natnael Yimer
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link