Sidakir Wulo

ሲዳክር ውሎ
ሲዳክር ውሎ
ሲዳክር ውሎ

ይነቃል ይነቃል ይነቃል መንፈሴ
በውሎ ግርግር የታወከው ነፍሴ
ሲወጣና ሲወርድ ዝሎ ይውልና
አንቺን አይቶ ይበረታል ይታደሳል እንደገና

ሲታትር ውሎ ለኑሮ ሲለፋ
ሲጥር ሲጭር ውሎ ቀኑን እየገፋ
የድግምግሞሽ ህይወቱ ተስፋው ሚታደሰው
ዙረቱ ሚቀለው ባንቺው መኖር ነው
ሆነሽ ተጨማሪ ለምድር አዲስ ሰው
በረከቴ ሞላ ህይወቴን አደመቅሽው
በዕለቱ ኑሮዬ ዝዬም እንዳልወቅሰው

ሲዳክር ውሎ ሲዳክር ውሎ
ሲዳክር ውሎ ሲዳክር ውሎ (ሰው)
ሲዳክር ውሎ ሲዳክር ውሎ
ሲዳክር ውሎ ሲዳክር ውሎ (ሰው)

ሲገባ ሲገባ ከቤቱ
ያኔ ነው የሚበራው ፊቱ
የዛለው ድካም ሁሉ ጥሶ
ይበረታል እንደ አዲስ መልሶ
ሲገባ ሲገባ ከቤቱ
ያኔ ነው የሚበራው ፊቱ
የዛለው ድካም ሁሉ ጥሶ
ይበረታል እንደ አዲስ መልሶ

ሆነሽ ተጨማሪ ለምድር አዲስ ሰው
በረከቴ ሞላ ህይወቴን አደመቅሽው
በዕለቱ ኑሮዬ ዝዬም እንዳልወቅሰው
ደገመና ባንቺ የእኔን ቤት አበራው

ሲገባ ሲገባ ከቤቱ
ያኔ ነው የሚበራው ፊቱ
የዛለው ውበት ሁሉ ጥሶ
ይበረታል እንደ አዲስ መልሶ
ሲገባ ሲገባ ከቤቱ
ያኔ ነው የሚበራው ፊቱ
የዛለው ጉልበት ሁሉ ጥሶ
ይበረታል እንደ አዲስ መልሶ

በረከቱን ቆጥሮ ካጣው ሚበልጠውን
ክፋቷን ይንቃል የአለምን ሲሰማ የዋለውን
የሚኖርለትን ምክንያቱን ያይና
በተስፋ ይነሳል ጀግኖ እንደገና
የኑሮ ውጣ ውረድ አይፈትን አይረታው
ጣፋጭ ነው መራራው አይኑን ባይኑ ላየው
የኑሮ ውጣ ውረድ አይፈትን አይረታው
ጣፋጭ ነው መራራው አይኑን ባይኑ ላየው

የኑሮ ውጣ ውረድ አይፈትን አይረታው
ጣፋጭ ነው መራራው አይኑን ባይኑ ላየው

I want Baby Shark
You want Baby Shark? Ok!



Credits
Writer(s): Natnael Yimer
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link