Zim Atabzi

ወይ መታደል ውበት ያደላት ለዛን ጨምሮ
ይናፍቃል አንደበቷ ማር አይሰለች አድሮ
በይ ተጫወች እንደ ልማድሽ ሁሉን አፍዢ
ወርቅ አይደለም ባንቺ ነሀስ ነው ዝምታ አታብዢ
ወይ መታደል ውበት ያደላት ለዛን ጨምሮ
ይናፍቃል አንደበቷ ማር አይሰለች አድሮ
በይ ተጫወች እንደ ልማድሽ ሁሉን አፍዢ
ወርቅ አይደለም ባንቺ ነሀስ ነው ዝምታ አታብዢ

እንዲህ ነው መታደል እንዲህ ነው ተፈጥሮ
ማይጠገብ ለዛ ሲያወራ ውሎ አድሮ
ዝምታ ወርቅ ነው ሲባል የነበረ
ለካስ ጨዋታ ነው ከወርቅ የከበረ

ብርሃን አድርጎሽ
ሁሉን አድማቂ
አስኪ ተጫወች
ቤቱን አድምቂ
ሲሰማሽ ውሎ
ሰው በዝምታ
ቀልቡን ያጣዋል
የማታ ማታ

ባንቺ አየን የአንድዬን ስራ
ያለ እንከን እንደሚሰራ
ፈጣሪ ተራቆብሻል
ጥበቡን ማሳያ አርጎሻል
ባንቺ አየን የአንድዬን ስራ
ያለ እንከን እንደሚሰራ
ፈጣሪ ተራቆብሻል
ጥበቡን ማሳያ አርጎሻል

ወይ መታደል ውበት ያደላት ለዛን ጨምሮ
ይናፍቃል አንደበቷ ማር አይሰለች አድሮ
በይ ተጫወች እንደ ልማድሽ ሁሉን አፍዢ
ወርቅ አይደለም ባንቺ ነሀስ ነው ዝምታ አታብዢ
ወይ መታደል ውበት ያደላት ለዛን ጨምሮ
ይናፍቃል አንደበቷ ማር አይሰለች አድሮ
በይ ተጫወች እንደ ልማድሽ ሁሉን አፍዢ
ወርቅ አይደለም ባንቺ ነሀስ ነው ዝምታ አታብዢ

ምን ተሰጥቶሽ ውበት ከሰው የተለየ
ሁሉም ፈዞ ቀረ ውበትሽን እያየ
መጣሪያ አጣሁልሽ ማን ልበልሽ ደሞ
ከምን ከምን ይሆን የሰራሽ ቀምሞ

ብርሃን አድርጎሽ
ሁሉን አድማቂ
አስኪ ተጫወች
ቤቱን አድምቂ
ሲሰማሽ ውሎ
ሰው በዝምታ
ቀልቡን ያጣዋል
የማታ ማታ

ባንቺ አየን የአንድዬን ስራ
ያለ እንከን እንደሚሰራ
ፈጣሪ ተራቆብሻል
ጥበቡን ማሳያ አርጎሻል
ባንቺ አየን የአንድዬን ስራ
ባንቺ አየን የአንድዬን ስራ
ያለ እንከን እንደሚሰራ
ፈጣሪ ተራቆብሻል
ጥበቡን ማሳያ አርጎሻል
ባንቺ አየን የአንድዬን ስራ
ያለ እንከን እንደሚሰራ
ፈጣሪ ተራቆብሻል
ጥበቡን ማሳያ አርጎሻል
ባንቺ አየን የአንድዬን ስራ



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Eiyubel B Birhanu, Henok Negash
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link