Wodijesh Neber

እኔስ ተሳስቼ ወድጄሽ ነበረ (ወድጄሽ ነበረ)
አንቺም ትተሺኛል እኔም ተውኩሽ ቀረ (እኔም ተውኩሽ ቀረ)
እኔስ ተሳስቼ ወድጄሽ ነበረ (ወድጄሽ ነበረ)
አንቺም ትተሺኛል እኔም ተውኩሽ ቀረ (እኔም ተውኩሽ ቀረ)

የምስራች ስትይ ማታለል አወቀ
ማታለል ኣወቀ
እንዳልናፈቀ ሰው እንዳልተጨነቀ
እንዳልተጨነቀ
ፍሪንባ ላኪልኝ በኪስ አገልግል
በኪስ አገልግል
እኔ አንጀት አልበላም አንቺን ይመስል
አንቺን ይመስል

እኔስ ተሳስቼ ወድጄሽ ነበረ (ወድጄሽ ነበረ)
አንቺም ትተሺኛል እኔም ተውኩሽ ቀረ (እኔም ተውኩሽ ቀረ)

ከእንግዲህ አልበላም ብርቱካኔን ልጬ
ብርቱካኔን ልጬ
መለየት እያለ ከጎኔ አስቀምጬ
ከጎኔ ኣስቀምጬ
እወየው ግልግል ቀለለልኝ እዳ
ቀለለልኝ እዳ
አብሬ ኖራለው ብዬ ስሰናዳ
ብዬ ስሰናዳ
እመነኩሳለው እገባለው ገዳም
እገባለው ገዳም
ደግሞ ለስጋዬ በነፍሴ አልጎዳም
በነፍሴ አልጎዳም

እኔስ ተሳስቼ ወድጄሽ ነበረ (ወድጄሽ ነበረ)
አንቺም ትተሺኛል እኔም ተውኩሽ ቀረ (እኔም ተውኩሽ ቀረ)
እኔስ ተሳስቼ ወድጄሽ ነበረ (ወድጄሽ ነበረ)
አንቺም ትተሺኛል እኔም ተውኩሽ ቀረ (እኔም ተውኩሽ ቀረ)

እኔስ ተሳስቼ ወድጄሽ ነበረ (ወድጄሽ ነበረ)
አንቺም ትተሺኛል እኔም ተውኩሽ ቀረ (እኔም ተውኩሽ ቀረ)

አንቺም በዛ ብትሄጅ እኔም በዚያ ሄድኩኝ
እኔም በዚያ ሄድኩኝ
ብድሬንም መለስኩ ህመሜንም ዳንኩኝ
ህመሜንም ዳንኩኝ
እንዴት እደርጋለው የዛቺን ልጅ ነገር
የዛቺን ልጅ ነገር
ባይኔ ዉሃ ሞላ ወንዙን ሳልሻገር
ወንዙን ሳልሻገር
ያ ሁሉ ደስታ ተቀይሮ ዛሬ
ተቀይሮ ዛሬ
ሃዘን ሰፈነበት በፍቅርሽ በፍቅሬ
በፍቅርሽ በፍቅሬ
ማነው የሚረዳው ማነው የሚሰማው
ማነው የሚሰማው
በሰው ላይ ሰው መውደድ የደረሰበት ሰው
የደረሰበት ሰው

እኔስ ተሳስቼ ወድጄሽ ነበረ (ወድጄሽ ነበረ)
አንቺም ትተሺኛል እኔም ተውኩሽ ቀረ (እኔም ተውኩሽ ቀረ)



Credits
Writer(s): Traditional
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link