Minew Shewa

ምነው ሸዋ - አብዱ ኪያር

ቢቀር ይቅር ቢቀር ይቅር እንጂ ምቾቴ
መክበር አልፈልግም እኔስ በብልጠቴ
ብኖር ይሻለኛል ከነቅንነቴ
ቢቀር ይቅር ቢቀር ይቅር እንጂ ምቾቴ
መክበር አልፈልግም እኔስ በብልጠቴ
ብኖር ይሻለኛል ከነድህነቴ

በስፍር በቁጥር ላልተወሰነ እድሜ ላልተወሰነ እድሜ
አልፈልግም መኖር ባቋራጭ ቀድሜ ባቋራጭ ቀድሜ
ለመኖር ልብላ እንጂ ልበላስ አልኖርም ልበላስ አልኖርም
ብትጠሉም ጥሉኝ ቃሌ አይቀየርም ቃሌ አይቀየርም

የሆዴን ነገር ብረሳ
ለህሊናዬ ብገዛ
የዋህነቴን ባበዛ
ሞኝ ነህ አሉኝ ፈዛዛ
እምነቱን ብሎ የኖረ
ፍቅሩን ይዞ ያደረ
ልቡን ለእውነት የሰዋ
ሞኝ ይባላል ወይ ሸዋ
ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ
ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ

ምነው ሸዋ ፍቅር ከውስጥ እንጂ ከነፍስ
መች ተገኝቶ ያቃል ውጪው ቢታሰስ
ልብ ይቀርብ የለም ወይ ከሰው ሰራሽ ኪስ
ምነው ሸዋ ፍቅር ከውስጥ እንጂ ከነፍስ
መች ተገኝቶ ያቃል ውጪው ቢታሰስ
ልብ ይቀርብ የለም ወይ ከሰው ሰራሽ ኪስ

ማለፍ እንኳን ቢቻል እውነትን ረጋግጦ እውነትን ረጋግጦ
እንዴት ነው ሚኖረው ከጸጸት አምልጦ ከጸጸት አምልጦ
የዛሬን ለመኖር ማስመሰል አልችልም ተውኝ እኔ አልችልም
ለማይረባ ጸሎት እኔ አሜን አልልም እኔ አሜን አልልም

የሆዴን ነገር ብረሳ
ለህሊናዬ ብገዛ
የዋህነቴን ባበዛ
ሞኝ ነህ አሉኝ ፈዛዛ
እምነቱን ብሎ የኖረ
ፍቅሩን ይዞ ያደረ
ልቡን ለእውነት የሰዋ
ሞኝ ይባላል ወይ ሸዋ
ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ
ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ
ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ ምነው ሸዋ



Credits
Writer(s): Abdu Kahssay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link