Dagnaw

ክፉ ና ደጉን ሳናውቅ
በልጅነት ህይወት
ኩልትፍትፍ ባለ አንደበት
መፈንደቅ መጫወት
ግጥማችን ቤት አይመታ
ስርዓቱንም አናውቀው
በጭብጨባ ነበረ ሰፈሩን ምናደምቀው
(ዳኛው) ተረሳሽ ወይ (ዳኛው)
እኔ ላስታውስሽ (ዳኛው)
እቅፍ አድርጌ (ዳኛው) ማጫውትሽ (ዳኛው)
እኔ እና አንቺን (ዳኛው) ያጣመረን (ዳኛው)
ዘፈን ነበር (ዳኛው) ያፋቀረን (ዳኛው)
አደግንና (ዳኛው) ተቀየረ (ዳኛው)
መፍራት ማፈር (ዳኛው) ተጀመረ(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
ሄሄ.(ዳኛው) አሃሃ.(ዳኛው)
አሄሄ(ዳኛው)
ፍቅርሽ በልጅነት ያኔ ተጀምሮ
እያሰቃየኝ ነው አድጎ ና ጨምሮ(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) እድሜ ዳኛው
የልቤን ገልጨ መናገር ጨንቆኛል
እድሜ ግልፅነቴን ከላዬ ነጥቆኛል(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
ከሀ-ግዕዝ ለ ግስ በ ፊት
አሊፍአ ሳንል
ዘፈን ነበር ምናውቀው ሳናጠና ፊደል
መቼም ከልቤ አይጠፋ ያምንወደው ጭፈራ
ጮክ ብለን ምንዘፍነው በነፃነት ሳንፈራ
(ዳኛው) ተረሳሽ ወይ (ዳኛው)
እኔ ላስታውስሽ (ዳኛው)
እቅፍ አድርጌ (ዳኛው) ማጫውትሽ (ዳኛው)
ዘፈን ነበር (ዳኛው) ያጣመረን (ዳኛው)
እኔ እና አንቺን (ዳኛው) ያፋቀረን (ዳኛው)
አደግንና (ዳኛው) ተቀየረ (ዳኛው)
መፍራት ማፈር (ዳኛው) ተጀመረ(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
ሄሄ.(ዳኛው) አሃሃ.(ዳኛው)
አሄሄ(ዳኛው)
አቅፌ ልስምሽ ልቤ ይከጅልና
እንዴት ብዬ ላርገው ሆነብኝ ፈተና
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
ገና አይንሽን ሳየው እጨናነቃለሁ
እድሜ ነፃነቴን ወስዶት እፈራለሁ
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
ከተሰማንም ዘፍነን በየዋህነት የኖርነው
ድሮ ልብ ሳንገዛ በልጅነት እድሜ ነው
ግልፅነት እና እውነት ስሜታችን ላይ ነበር
ልብ ስንገዛ ጠፋ አቤት የግዢ ነገር
(ዳኛው) የላይኛው(ዳኛው) ፍቅር ሰጠን(ዳኛው)
ነፃነትን (ዳኛው) አለበሰን (ዳኛው)
የምድሩ (ዳኛው) የታችኛው(ዳኛው)
ወረደብን(ዳኛው) እድሜ ዳኛው (ዳኛው)
አደግንና (ዳኛው) ተቀየረ (ዳኛው)
መፍራት ማፈር (ዳኛው) ተጀመረ(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
ሄሄ.(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) ሄሄ.(ዳኛው)
አንቺንም እንደኔ ያደርግሻል ወይ
የልብን መናገር ያስፈራሻል ወይ(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
ስሜቴ በሙሉ አፍቅራት ይለኛል
ውድድ ውድድ አርጋት አተዋት ይለኛል(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) እድሜ ዳኛው(ዳኛው)
ሄሄ.(ዳኛው)
እድሜ ዳኛው(ዳኛው) ሄሄ.(ዳኛው)
...(ዳኛው)...



Credits
Writer(s): Abdu Kahssay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link