Athidibgn (feat. Jossy Kassa)

ሁልጊዜ ምናፍቅህ
የነፍሴ ጥማት የምትወድህ
ልዑል ነህ ለእኔ
እርሱ ነው ረሃቤ

ያለ አንተ መኖር አልችልም
ታውቃለህ አቅም እኔ የለኝም
ኢየሱሴ የእኔ
አትሂድብኝ ከእኔ

አዝ፦ አትሂድብኝ ደካማ ነኝ
ያለ አንተማ አቅም የለኝም

ባጠፋም ልጅህ ነኝ ቅጣኝ
ግን መንፈስህ እንዳይርቀኝ
የሕይወት እስትንፋሴ
ህልውናህ ነው ኢየሱሴ

ስትርቀኝ ይከፋኛል
አንተን መፍራት ይከብደኛል
የምትረዳኝ ረድኤቴ
አትሂድ ከሕይወቴ

አዝ፦ አትሂድብኝ ደካማ ነኝ
ያለ አንተማ አቅም የለኝም

ዝናህ ሀብት ሞልቶ ጐተራዬም ቢሞላም አዬ
መኖር አልችልም እኔ ስትለየኝ ከጐኔ

መኖር ይከብደኛል ሕይወትም ይታክተኛል
መኖር አልችልም እኔ ስትለየኝ ከጎኔ

አባብዬ የእኔ ጌታ ናፍቆቴ ነህ ጠዋትም ማታ
ህልውናህ መገኘት ደስታን አጠገበኝ ፊትህ

ፊትህን ሳየው ውስጤን ደስታ ትሞላኛለህ
ምንም ባይኖረኝ ምንም አንተው ትበቃኛለህ

መኖር አልችልም እኔ ስትለየኝ ከጐኔ
መኖር አልችልም እኔ ስትለየኝ ከጐኔ



Credits
Writer(s): Simone Tsegay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link