Selam

ዋሽቶ ለመኖር አፌ አይችልም ከቶ
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም
ገንዘብ ለማግኝት ብዬ አላጣም ሰላም
እኔ አላጣም ሰላም
አላጣም ሰላም
እኔ አላጣም ሰላም
ይህ ዓለም ንዋይ ጭኖ ወርቁን በሙዳይ
ማርኮት ከረታት ነፍሴን ከሰጣት ጉዳይ
ህሊና ሲያጣ ሰላም ወርቅ አልማዝ ሞልቶ
ሳይተኙ ማደር ሊሆን ከራስ ተጣልቶ
ከዚህ ሁሉ ቅጣት
ይሻላል ማጣት
አስኮንኛት ነፍሴን
አልሞላም ኪሴን
ነፍሴ እጅ እንዳትሰጪው ለኪሴ
ታጣይኛለሽ ከራሴ
ሰላሜ እረፍት ያለብሽ መኝታ
ታምነሽ አኑሪኝ ከጌታ
አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
ያሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን
አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
ይሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን
ባዶ ላርገው ኪሴን
ባዶ ላርገው ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን
ዋሽቶ ለመኖር አፌ አይችልም ከቶ
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም
ይሄን ለማግኘት ብዬ አላጣም ሰላም
እኔ አላጣም ሰላም
አላጣም ሰላም
እኔ አላጣም ሰላም
የአመል ነው እንጂ ደሃ የገንዘብ የለም
ሰው ባይኖር እይዋት እራሷን ባዶ ናት አለም
ገንዘብ ብቻ ነው ያለም የዚህ አለም ደስታ
ዳግም ይሸጣል ስሞ ቢመለስ ጌታ
ለሰላሣ ዲናር
ሊያጣ ነብስ ይማር
አስኮንኛት ነፍሴን
አልሞላም ኪሴን
ነፍሴ እጅ እንዳትሰጪ ለኪሴ
ታጣይኛለሽ ከራሴ
ሰላሜ እረፍት ያለብሽ መኝታ
ታምነሽ አኑሪኝ ከጌታ
አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
ይሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን
አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
ይሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን
ባዶ ላርገው ኪሴን
ባዶ ላርገው ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን
አ...
ባዶ!
አ...
ባዶ!
አ...
ባዶ!
አ...
ባዶ!
አ...
ባዶ!



Credits
Writer(s): Fred Jr. Scruggs, Kirk Jones, Chylow M. Parker, Tyrone Taylor, Jason William Mizell
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link