Suse Nesh

ብሄድ አይመቸኝ እኔን ብቀመጥ አይደላህኝ
ባካል አይመቸኝ እኔን በመንፈስ አይደላኝ
የቀን ቅዠት ህልሜ ሆነሻል
ሳስብሽ ሳነሳሽ ይመሻል
የቀን ቅዠት ህልሜ ሆነሻል
ሳስብሽ ሳነሳሽ ይመሻል

ብሄድ አይመቸኝ እኔን ብቀመጥ አይደላህኝ
ባካል አይመቸኝ እኔን በመንፈስ አይደላኝ
የቀን ቅዠት ህልሜ ሆነሻል
ሳስብሽ ሳነሳሽ ይመሻል
የቀን ቅዠት ህልሜ ሆነሻል
ሳስብሽ ሳነሳሽ ይመሻል

የንጋት ቅዠት ነሽ የማይቻል አቅም
ህይወቴ የነፍሴን አላውቅም
አትነኪ ክልክል አንቺ የበለስ ፍሬ
ቢሆን ብዬ እኮ ነው መቸገር መጣሬ
እንዳልቀር ጭንቀቴ በዛ
እንዳልሄድ ፍቅርሽ መች የዋዛ
ላጣሁሽ ይብላኝ ለራሴ
ሱሴ ነሽ ናፍቆቴ ምሴ
እንዳልቀር ጭንቀቴ በዛ
እንዳልሄድ ፍቅርሽ መች የዋዛ
ላጣሁሽ ይብላኝ ለራሴ
ሱሴ ነሽ ናፍቆቴ ምሴ
ጭንቀቴ ለፍቅርሽ በዋለ
ትዝታሽ በልቤ ዋለለ
አምኜሽ ፍቅርን በረዳሁኝ
ተጎዳሁኝ
አዝኜ ይከፋሻል ብዬ
ሆድዬ ፍቅሬን በሰው በሰው
አልፈልግም እንደበደለ ሰው

ብሄድ አይመቸኝ እኔን ብቀመጥ አይደላህኝ
ባካል አይመቸኝ እኔን በመንፈስ አይደላኝ
የቀን ቅዠት ህልሜ ሆነሻል
ሳስብሽ ሳነሳሽ ይመሻል
የቀን ቅዠት ህልሜ ሆነሻል
ሳስብሽ ሳነሳሽ ይመሻል

ብሄድ አይመቸኝ እኔን ብቀመጥ አይደላህኝ
ባካል አይመቸኝ እኔን በመንፈስ አይደላኝ
የቀን ቅዠት ህልሜ ሆነሻል
ሳስብሽ ሳነሳሽ ይመሻል
የቀን ቅዠት ህልሜ ሆነሻል
ሳስብሽ ሳነሳሽ ይመሻል

ከተስፋሽ እርቄ ከምኞትሽ ወጣው
አንቺም ሄድሽ እርቀሽ ፍቅርሽንም አጣው
ውስጤ እየነደደ በትዝታ ረመጥ
በቃልሽ ታስሬ መች ደላኝ ብቀመጥ
እንዳልቀር ጭንቀቴ በዛ
እንዳልሄድ ፍቅርሽ መች የዋዛ
ላጣሁሽ ይብላኝ ለራሴ
ሱሴ ነሽ ናፍቆቴ ምሴ
እንዳልቀር ጭንቀቴ በዛ
እንዳልሄድ ፍቅርሽ መች የዋዛ
ላጣሁሽ ይብላኝ ለራሴ
ሱሴ ነሽ ናፍቆቴ ምሴ
ደስታዬ በኑሮሽ ከብሬ
እንዳይሽ ምክንያቶች ፈጥሬ
በርቀት በናፍቆት አታጥቂኝ
አትራቂኝ
ጭንቀቴ ዋጋ ሳያወጣ
ልፋቴ ናፍቆት ይዞ መጣ
ጥረቴ ነበር እንዳይከፋሽ
መውደዴ ማፍቀሬ መች ገባሽ
ጭንቀቴ በፍቅርሽ በዋለ
ትዝታሽ በልቤ ዋለለ
አምኜሽ ፍቅርን በረዳሁኝ
ተጎዳሁኝ
አዝኜ ይከፋሻል ብዬ
ሆድዬ ፍቅሬን በሰው በሰው
አልፈልግም እንደበደለ ሰው



Credits
Writer(s): Alemtsehay Wedajo, Moges Teka
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link