Aba Alem Lemenea

አባ አለም ለምኔ አባ አለም ለምኔ
ጀምበር ወታ አትገባም ሳልሰራ ኩነኔ
አባ አለም ለምኔ አባ አለም ለምኔ
ጀምበር ወታ አትገባም ሳልሰራ ኩነኔ

ሰው ወደድኩኝ እያልኩ ደ'ሞ እጠላለው
ደ'ሞ ይከፋኛል እደሰታለው
ዛሬ ቀጭን ኩታ ነገ ራቁቴን
አገኘው ስል ወዳጅ ደግሞ ማጣትን
ደ'ሞ ማጣትን
አባ አለም ለምኔ አባ አለም ለምኔ
ጀምበር ወታ አትገባም ሳልሰራ ኩነኔ
አባ አለም ለምኔ አባ አለም ለምኔ
ጀምበር ወታ አትገባም ሳልሰራ ኩነኔ

አባ አለም ለምኔ ለምን ለምን ለምን
አባ አለም ለምኔ ደግሞ ለምን ይክፋኝ
አባ አለም ለምኔ ለምን ለምን ለምን
አባ አለም ለምኔ ደግሞ ለምን ይክፋኝ
ብስጭት ጭንቀት ጤንነት አይሆነኝ
ብስጭት ጭንቀት ጤንነት አይሆነኝ

ሰው በአፉ እያነሳ በእጁ ይጥለኛል
የልቡን አላውቅም ግራ ይገባኛል
የልብን ጥያቄ ማነው የሚፈታ
ካንተ በቀር አባት ካንተ በቀር ጌታ
ዛሬ ጥያቄ አለኝ
ለምን ለምን ለምን ደግሞ ለምን ይክፋኝ
ብስጭት ጭንቀት ጤንነት አይሆነኝ
ብስጭት ጭንቀት ጤንነት አይሆነኝ

ደስታን ስጠኝ ለህይወቴ
አይሳንህምና አባቴ
አርቅልኝ ክፉውን
እንዳልማር ክፋቱን
በቀኝ አውለህ አሳድረኝ
ክፋ ነገር ሳይወጣኝ
ሳይወጣኝ ክፉ ነገር ሳይወጣኝ
ምን ሊሰራልኝ ጥላቻ ሀሜት
ሀብት አይሆነኝም ቤት አልሰራበት
ልብ ያጨልማል ክፉነገር
ልቤን አብሩልኝ ስጡኝ ፍቅር

አባ 'ለም ለምኔ
ጀምበር ወጥታ አትገባም ሳልሰራ ኩነኔ



Credits
Writer(s): Ejigayehu Shibabaw
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link