Sigibgib Joroye

ስግብግብግብግብግብግብግብ አለች ጆሮዬ
ስግብግብግብግብግብግብግብ አለች ጆሮዬ

ጎጂ ጠቃሚውን (እያጣራ ይስማ)
እያግበሰበሰ (ስግብግብ ጆሮዬ)
ከጤናዬ ተርፎ (እያጣራ ይስማ)
ቤቴን አፈረሰ (ስግብግብ ጆሮዬ)
ልክስክሱን ሁሉ (እያጣራ ይስማ)
እያጠራቀመ (ስግብግብ ጆሮዬ)
ይኸው እስከዛሬ (እያጣራ ይስማ)
አንጀቴ ታመመ (ስግብግብ ጆሮዬ)

ሰው ሁሉ እንዳይሆን ፍፁም ደመኛዬ
እያጣራ ይስማ ስግብግብ ጆሮዬ
ሰው ሁሉ እንዳይሆን ፍፁም ደመኛዬ
እያጣራ ይስማ ስግብግብ ጆሮዬ

(ስግብግብግብግብግብግብግብ አለች ጆሮዬ)

ለስቃይ የሚደርስ (እያጣራ ይስማ)
መሳይ ተቆርቋሪ (ስግብግብ ጆሮዬ)
ይሄ ጉድን ፍጡር (እያጣራ ይስማ)
መንፈስ አሸባሪ (ስግብግብ ጆሮዬ)
ይስማ እንጂ ጆሮዬ (እያጣራ ይስማ)
ባስቀርስ ቀጥቼ (ስግብግብ ጆሮዬ)
መጥፎውን ከጥሩ (እያጣራ ይስማ)
ይለያሉ ዐይኖቼ (ስግብግብ ጆሮዬ)

ሰው ሁሉ እንዳይሆን ፍፁም ደመኛዬ
እያጣራ ይስማ ስግብግብ ጆሮዬ
ሰው ሁሉ እንዳይሆን ፍፁም ደመኛዬ
እያጣራ ይስማ ስግብግብ ጆሮዬ

(ስግብግብግብግብግብግብግብ አለች ጆሮዬ)

ስንት አለ በቤቱ (እያጣራ ይስማ)
ሆዱ ያላረረ (ስግብግብ ጆሮዬ)
ክፉ ነገር ሰምቶ (እያጣራ ይስማ)
ተኝቶ ያደረ (ስግብግብ ጆሮዬ)
ዘልቆ ሳይረዳ (እያጣራ ይስማ)
የጆሮን ምስጢር (ስግብግብ ጆሮዬ)
ጥላቻን ያተርፋል (እያጣራ ይስማ)
ፍጡር በፍጡር (ስግብግብ ጆሮዬ)

ሰው ሁሉ እንዳይሆን ፍፁም ደመኛዬ
እያጣራ ይስማ ስግብግብ ጆሮዬ
ሰው ሁሉ እንዳይሆን ፍፁም ደመኛዬ
እያጣራ ይስማ ስግብግብ ጆሮዬ



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Tezera H. Michael
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link