Bezih Alem (feat. Samuel Negussie)

በዚህ ፡ ዓለም ፡ ምን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ነገር ፡ አለ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንደመኖር
በዚህ ፡ ምድር ፡ ምን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ነገር ፡ አለ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንደመኖር
እወደዋለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ እወደዋለሁ
እወደዋለሁ ፡ መኖሬን ፡ እወደዋለሁ
እወደዋለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ እወደዋለሁ
እወደዋለሁ ፡ መኖሬን ፡ እወደዋለሁ
ሳስበው ካ'ንተ ጋር እንዳለሁ (3×)
ሳስበው ሁሌ እደሰታለሁ፤
በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ያለ ፡ የህይወት ፡ ቃል
ሌላ ፡ ስፍራ ፡ የትም ፡ 'ማላገኘው
ብር ፡ የማይሰጠኝ ፡ ወርቅ ፡ የማይሰጠኝ
የሕይወቴን ፡ አቅጣጫ ፡ የለወጠው፤
የሁልጊዜ ፡ ነው ፡ የልቤ ፡ ሰላም
ከመንፈስህ ፡ ከቃልህ ፡ የመነጨው
በዚህ ፡ አለም ፡ ነገር ፡ የማይወሰን
የእኔን ፡ ሕይወት ፡ የደስታ ፡ ያደረገው
ብዙ ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ በሕይወቴ
ብዙ ደስታ አለ፤
ብዙ ፡ ሰላም ፡ አለ ፡ በሕይወቴ
ብዙ ሰላም አለ፤
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ስላለ
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በእኔ ፡ ውስጥ ፡ ስላለ
ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ስላለ
መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ ስላለ
ሸክም ፡ የከበደው ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ይምጣ
ይረፍ ፡ ብለህ ፡ የጠራኸኝ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ
ሁሉንም ፡ ነገር ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼ
እፎይ ፡ ብዬ ፡ ተደላድዬ ፡ ምኖርብህ
ኢየሱስ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ያለኝ ፡ ህብረት
ማለት ፡ ለእኔ ፡ አለሜ ፡ ነው፥ አለሜ ነው
ለሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ያገኘሁበት
ምክንያቱ ፡ ነው ፡ የዘላለሜ ፡ የሰመረበት
በዚህ ፡ ዓለም ፡ ምን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ነገር ፡ አለ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንደመኖር
በዚህ ፡ ምድር ፡ ምን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ነገር ፡ አለ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንደመኖር
እወደዋለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ እወደዋለሁ
እወደዋለሁ ፡ መኖሬን ፡ እወደዋለሁ
እወደዋለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ እወደዋለሁ
እወደዋለሁ ፡ መኖሬን ፡ እወደዋለሁ
ሳስበው ካ'ንተ ጋር እንዳለሁ (3×)
ሳስበው ሁሌ እደሰታለሁ፤

writer- Mignot Dansa



Credits
Writer(s): Simone Tsegay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link