Des Alew Liben

ስፈራ ስቸር ቆይቼ
ላሳያት ውስጤን ስሜቴን
በፍቅር ባታስበኝስ
ቢለኝ ስጋቴ ደፍሬው ጭንቀቴን
ደስ አለው ልቤን ነገርኳት
እሷም እንደኔ ፍቅር አላት
ምወዳት ወዳኝ ተገኝታ
እኔን ልቧ ፈቀደና
ሰመረ ፍቅር ፀና
ደስ አለው ልቤን ነገርኳት
እሷም እንደኔ ፍቅር አላት
ወዶ መወደድ ሆነና
እኔን ልቧ ፈቀደና
ሰመረ ፍቅር ፀና
እንዳይቀር ብዬ እህትነቷ
ስፈራ ስቸር ኖሬ ኖሬ
ጭራሽ በፍቅር እናት ሆነችኝ
ምወዳት ቆንጆ ተቀበለችኝ
ልመርቃችሁ እንዲ እያልኳችሁ
የምትወዱት ይውደዳችሁ
ጭንቀታችሁ ይቅለላችሁ
ይሁን ሙሉ ሰላማችሁ
ስፈራ ስቸር ቆይቼ
ላሳያት ውስጤን ስሜቴን
በፍቅር ባታስበኝስ
ቢለኝ ስጋቴ ደፍሬው ጭንቀቴን
ደስ አለው ልቤን ነገርኳት
እሷም እንደኔ ፍቅር አላት
ምወዳት ወዳኝ ተገኝታ
እኔን ልቧ ፈቀደና
ሰመረ ፍቅር ፀና
ደስ አለው ልቤን ነገርኳት
እሷም እንደኔ ፍቅር አላት
ወዶ መወደድ ሆነና
እኔን ልቧ ፈቀደና
ሰመረ ፍቅር ፀና
ቀርቼ ብሆን ፍቅሬን ሳልነግራት
ይቆጨኝ ነበር ከሰው ባያት
ያያት ነው ቅርሷ ሴትነት ይዟት
ከሱ ይምጣ እያለች ነበር ላጣት
ካለመናገር ደጃዝማችነት
ይቀር የለ ወይ ፍቅርም ሹመት
ልመርቃችሁ እንዲ እያልኳችሁ
የምትወዱት ይውደዳችሁ
ጭንቀታችሁ ይቅለላችሁ
ይሁን ሙሉ ሰላማችሁ
ደስ አለው ልቤን ነገርኳት
እሷም እንደኔ ፍቅር አላት
ምወዳት ወዳኝ ተገኝታ
እኔን ልቧ ፈቀደና
ሰመረ ፍቅር ፀና
ደስ አለው ልቤን ነገርኳት
እሷም እንደኔ ፍቅር አላት
ወዶ መወደድ ሆነና
እኔን ልቧ ፈቀደና
ሰመረ ፍቅር ፀና።



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Meraf Asefa
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link