Ye Kistos Demtsu

በርጠሚዮስ ነኝ አይነ ስዉር ምስኪን
በሩቅ የሰማሁት የጌታዬን ድምጹን
ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሃል
የክርስቶስ ድምጹ በግልጽ ይሰማኛል
የክርስቶስ ድምጹ በግልጽ ይሰማኛል

የልቦናዬ አይን ፈጽሞ ታውሯል
አይኔን ፈዉስልኝ በርጠሚዮስ ይላል
አብዝቼ ጮሃለሁ ጌታ ማረኝ ብዬ
በዉስጤ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ
በዉስጤ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ

አንተን አይሰማህም ይሉኛል ብዙወች
በሃጺያት ሰንሰለት ታስረሃጥክተወች
ስለዚህ አትልፋ ሲኦልን ጠብቃት
አንደዚህ ቢሉኝም ጮሃለሁ ሳልታክት
አንደዚህ ቢሉኝም ጮሃለሁ ሳልታክት

በርጠሚዮስ ነኝ አይነ ስዉር ምስኪን
በሩቅ የሰማሁት የጌታዬን ድምጹን
ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሃል
የክርስቶስ ድምጹ በግልጽ ይሰማኛል
የክርስቶስ ድምጹ በግልጽ ይሰማኛል

የከበበዉን ሰው ገለል በሉ እያለ
በደሌን በደሙ ዋጋ እየከፈለ
ስለኔ የሞተው እየሱስ ይመጣል
የልቦናዬን አይን ገልጦ ያሳየኛል
የልቦናዬን አይን ገልጦ ያሳየኛል

አብዝቼ ጮሃለሁ ጌታ ማረኝ ብዬ
በግልጽ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ
በዉስጤ በደልስ ህዬወቴ ዝላለች
ባምላኬ ቸርነት ሂወት ካላገኘች
ባምላኬ ቸርነት ሂወት ካላገኘች

በርጠሚዮስ ነኝ አይነ ስዉር ምስኪን
በሩቅ የሰማሁት የጌታዬን ድምጹን
ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሃል
የክርስቶስ ድምጹ በግልጽ ይሰማኛል
የጌታዬ ድምጹ በግልጽ ይሰማኛል
የአምላኬ ድምጹ በግልጽ ይሰማኛል
የጌታዬ ድምጹ በግልጽ ይሰማኛል

End



Credits
Writer(s): Simone Tsegay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link