Lewitegn

ማደግ እሻለሁ አንተን መምሰል
ግን አቅቶኛል ክብሬን መጣል
የዚህ ዓለም ነገር ልቤን አድክሞት
ለአንተ እንዴት ልኑር ለሌላው ሳልሞት
የዚህ ዓለም ነገር ልቤን አዝሎት
ለአንተ እንዴት ልኑር ለሌላው ሳልሞት

ለውጠኝ ለውጠኝ ለውጠኝ
ለውጠኝ ለውጠኝ ለውጠኝ

ቃል ኪዳኔን ያጠፍኩኝ
ደካማ ሰው እኔ ነኝ
እንዲያው ያለሁ ለብ ብዬ
እጮሃለሁ እንዲህ ብዬ
ቃል ኪዳኔን ያጠፍኩኝ
ደካማ ሰው እኔ ነኝ
እንዲያው ያለሁ ለብ ብዬ
እጮሃለሁ እንዲህ ብዬ
እጄን ያዘኝና አስጠጋኝ
ወደ ራስህ ሳበኝ
እጄን ያዘኝና አስጠጋኝ
ወደ ራስህ ሳበኝ

ከካቻምናው የአምና ከአምናው የዘንድሮ
ሕይወቴ ካልታየ ስምህ በእኔ ከብሮ
መኖርስ ምንድነው ዘመን ማስቆጠሩ
እንዲያው መመላለስ ፍሬን ሳያፈሩ

ቃል ኪዳኔን ያጠፍኩኝ
ደካማ ሰው እኔ ነኝ
እንዲያው ያለሁ ለብ ብዬ
እጮሃለሁ እንዲህ ብዬ
ቃል ኪዳኔን ያጠፍኩኝ
ደካማ ሰው እኔ ነኝ
እንዲያው ያለሁ ለብ ብዬ
እጮሃለሁ እንዲህ ብዬ
እጄን ያዘኝና አስጠጋኝ
ወደራስህ ሳበኝ
እጄን ያዘኝና አስጠጋኝ
ወደራስህ ሳበኝ

የእምነት አባቶቼ አንተን አስከብረው
የክብርን ሞት አዩ በእምነታቸው ጸንተው
ፀጋህን አልብሰኝ አልኑር ተሸንፌ
ከሚጠፋው ዓለም ጸጸትን አትርፌ

ቃል ኪዳኔን ያጠፍኩኝ
ደካማ ሰው እኔ ነኝ
እንዲያው ያለሁ ለብ ብዬ
እጮሃለሁ እንዲህ ብዬ
ቃል ኪዳኔን ያጠፍኩኝ
ደካማ ሰው እኔ ነኝ
እንዲያው ያለሁ ለብ ብዬ
እጮሃለሁ እንዲህ ብዬ

እጄን ያዘኝና አስጠጋኝ
ወደራስህ ሳበኝ
እጄን ያዘኝና አስጠጋኝ
ወደራስህ ሳበኝ



Credits
Writer(s): Simone Tsegay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link