Enen Yaye

አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገዴን ፡ ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ፡ ጠላቴ ፡ ቆሞ
ድንገት ፡ እግዚአብሔር ፡ ክንዱን ፡ ዘረጋ
የጠላቶቼ ፡ ወገብ ፡ ተወጋ

አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገድ ፡ ቢዘጋ
በግራ ፡ በቀኝ ፡ እኔን ፡ ቢዋጋ
እጄን ፡ ይዞ ፡ መራኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ
አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገዴን ፡ ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ፡ ጠላቴ ፡ ቆሞ
ድንገት ፡ እግዚአብሔር ፡ ክንዱን ፡ ዘረጋ
የጠላቶቼ ፡ ወገብ ፡ ተወጋ

እኔን ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ ድብን ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
እኔን ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
እኔን ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ ድብን ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
እኔን ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
ድብን ፡ ይበል ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
ቅጥል ፡ ይበል ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ

እስቲ ፡ እንበል ፡ እልልታ
እስቲ ፡ እንበል ፡ እልልታ
ሞትን ፡ ድል ፡ ላደረገው ፡ ጌታ ፡ ይገባዋል ፡ እልልታ
እስቲ ፡ እንበል ፡ ሽብሸባ
እስቲ ፡ እንበል ፡ ሽብሸባ

ሞትን ፡ ድል ፡ ላደረገው ፡ ጌታ ፡ ይገባዋል ፡ ሽብሸባ
ይሞታል ፡ ብሎ ፡ ጠላት ፡ ሲያወራ
አይወርስም ፡ ብሎ ፡ ጠላት ፡ ሲያወራ
ይሞታል ፡ ብሎ ፡ ጠላት ፡ ሲያወራ
አይወርስም ፡ ብሎ ፡ ጠላት ፡ ሲያወራ

አሻገረኝ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነውና
አሻገረኝ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነውና
አሻገረኝ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነውና
አሻገረኝ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነውና
አልቆ ፡ ነበረ ፡ የኔ ፡ ጉዳይ
ጌታ ፡ ባይመጣ ፡ ወርዶ ፡ ከላይ

ወርዶ ፡ ከላይ
አትሞትም ፡ ብሎ ፡ ሞቴን ፡ ሰበረው
የሞትን ፡ መውጊያ ፡ ድል ፡ አደረገው
ድል ፡ አደረገው
አልቆ ፡ ነበረ ፡ የኔ ፡ ጉዳይ
ጌታ ፡ ባይመጣ ፡ ወርዶ ፡ ከላይ
ወርዶ ፡ ከላይ

አትሞትም ፡ ብሎ ፡ ሞቴን ፡ ሰበረው
የሞትን ፡ መውጊያ ፡ ድል ፡ አደረገው
ድል ፡ አደረገው
አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገዴን ፡ ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ፡ ጠላቴ ፡ ቆሞ
ጠላቴ ፡ ቆሞ
ድንገት ፡ እግዚአብሔር ፡ ክንዱን ፡ ዘረጋ
የጠላቶቼ ፡ ወገብ ፡ ተወጋ
ወገብ ፡ ተወጋ

አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገዴን ፡ ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ፡ ጠላቴ ፡ ቆሞ
ጠላቴ ፡ ቆሞ
ድንገት ፡ እግዚአብሔር ፡ ክንዱን ፡ ዘረጋ
የጠላቶቼ ፡ ወገብ ፡ ተወጋ
ወገብ ፡ ተወጋ

አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገድ ፡ ቢዘጋ
በግራ ፡ በቀኝ ፡ እኔን ፡ ቢዋጋ
እጄን ፡ ይዞ ፡ መራኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ
አታልፍም ፡ ብሎ ፡ መንገዴን ፡ ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ፡ ጠላቴ ፡ ቆሞ
ድንገት ፡ እግዚአብሔር ፡ ክንዱን ፡ ዘረጋ

የጠላቶቼ ፡ ወገብ ፡ ተወጋ
እኔንም ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ ድብን ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
እኔን ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
እኔንም ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ ድብን ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
እኔን ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
ድብን ፡ ይበል ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ
ቅጥል ፡ ይበል ፡ ጠላቴ ፡ እርር ፡ ይበል ፡ ጠላቴ

እስቲ ፡ እንበል ፡ እልልታ
እስቲ ፡ እንበል ፡ እልልታ
ሞትን ፡ ድል ፡ ላደረገው ፡ ጌታ ፡ ይገባዋል ፡ እልልታ
እስቲ ፡ እንበል ፡ ሽብሸባ
እስቲ ፡ እንበል ፡ ሽብሸባ
ሞትን ፡ ድል ፡ ላደረገው ፡ ጌታ ፡ ይገባዋል ፡ ሽብሸባ



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Ephrem Alemu
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link