Metichalehu

የአማልክት አምላክ ነህ የነገስታት ንጉስ
የሚመስልህ የሌለ የእግዚአብሄር ልጅ እየሱስ

አመልክሃለው

መጥቻለው በፊትህ ላመልክህ ነው
አስቀድሜ በእግርህ ስር እሰግዳለው
ቀና ብዬ አንተን ሳይ ተውበሃል
የምስጋና የክብርም ዘውድ ጭነሃል

እጨምራለው በሞገስ ላይ ሞገስ
ንጉሴ ሆይ ከዚህም በላይ ንገስ
ባማረ ዜማ በተዋበ እልልታ
ይድመቅ ዙፋንህ ተመለክ ተወደስ የኔ ጌታ

እኔማ አላውቅህም አምላኬ ትልቅ ነህ
ከአይምሮዬ በላይ ሆነ ማንነትህ

ከፍ ባለ ዙፋን ላይ የተቀመጥከው
ብርሃንን እንደልብስ የለበስከው
ማእረግህ ስልጣንህ የብቻ ነው
በሹመትህስ እንዳንተ ማነው

እጨምራለው በሞገስ ላይ ሞገስ
ንጉሴ ሆይ ከዚህም በላይ ንገስ
ባማረ ዜማ በተዋበ እልልታ
ይድመቅ ዙፋንህ ተመለክ ተወደስ የኔ ጌታ

እኔማ አላውቅህም አምላኬ ትልቅ ነህ
ከአይምሮዬ በላይ ሆነ ማንነትህ

በክብር ማነው እንዳንተ ክቡር ማነው
ኧረ ማነው እንዳንተ ያለ ማነው

በሞገስ ማነው እንዳንተ ሞገሳም ማነው
ኧረ ማነው እንዳንተ ያለ ማነው

በሃይል ማነው እንዳንተ ሃያል ማነው
ኧረ ማነው እንዳንተ ያለ ማነው

በስልጣን ማነው እንዳንተ ባለስልጣን ማነው
ኧረ ማነው እንዳንተ ያለ ማነው

ካማልክት ማነው እንዳንተ አምላክ ማነው
ኧረ ማነው እንዳንተ ያለ ማነው

በፍጹም የለም እንዳንተ ያለ የለም
አይኖርም የለም እንዳንተ ያለ የለም



Credits
Writer(s): Simone Tsegay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link