Bale Washintu

ያገሬን ልጅ አልኩኝ እሱን ባለዋሽንቱን
የወንዜን ልጅ አልኩኝ እሱን ሰምቼ ድምፁን
ያገሬን ልጅ አልኩኝ እሱን ባለዋሽንቱን
የወንዜን ልጅ አልኩኝ እሱን ሰምቼ ድምፁን

ጎንበስ ቀና እያለ አዝመራው ከፊቴ
ቁልቁል ሲወረወር ከማዶው ፏፏቴ
ዋሽንቱን ሲጫወት ልስልስ ባለ ዜማ
ደህና ሁን አሰኘኝ ደህና ሁን ከተማ

ከግራ ገብሱን ከቀኝ ስንዴውን
አቋርጬ አልፌ ሳየው ሸጋውን
ልቤን እያመሠው የዋሽንቱ ዜማ
ደህና ሁን አሰኘኝ ደህና ሁን ከተማ

አሆ እማምዬ ደህና ሁን ከተማ
አሆ እማምዬ ተሰነባበተኝ
አሆ እማምዬ ትሰማው የለም ወይ
አሆ እማምዬ ዋሽንቱ ሲጠራኝ
አሆ እማምዬ አንተ ያገሬ ልጅ
አሆ እማምዬ መዋያህ ከማማ
አሆ እማምዬ ወጣው ካንተ ላድር
አሆ እማምዬ ሠለቸኝ ከተማ

ያገሬን ልጅ አልኩኝ እሱን ባለዋሽንቱን
የወንዜን ልጅ አልኩኝ እሱን ሰምቼ ድምፁን
ያገሬን ልጅ አልኩኝ እሱን ባለዋሽንቱን
የወንዜን ልጅ አልኩኝ እሱን ሰምቼ ድምፁን

በለመለመው መስክ በወንዙ ዳርቻ
ዋሽንቱን ሲጫወት ሲተክዝ ለብቻ
ከጋራው ላይ ቆሜ ቁልቁል እያየሁት
በእርሱ ተማርኬ ከተማን ጠላሁት
ከግራ ገብሱን ከቀኝ ስንዴውን
አቋርጬ አልፌ ሳየው ሸጋውን
ልቤን እያመሠው የዋሽንቱ ዜማ
ደህና ሁን አሰኘኝ ደህና ሁን ከተማ

አሆ እማምዬ ደህና ሁን ከተማ
አሆ እማምዬ ተሰነባበተኝ
አሆ እማምዬ ትሰማው የለም ወይ
አሆ እማምዬ ዋሽንቱ ሲጠራኝ
አሆ እማምዬ አንተ ያገሬ ልጅ
አሆ ማምዬ መዋያህ ከማማ
አሆ እማምዬ ወጣው ካንተ ላድር
አሆ እማምዬ ሰለቸኝ ከተማ

ጎንበስ ቀና እያለን አዝመራው ከፊቴ
ቁልቁል ሲወረወር ከማዶው ፏፏቴ
ዋሽንቱን ሲጫወት ልስልስ ባለ ዜማ
ደህና ሁን አሰኘኝ ደህና ሁን ከተማ

ያገሬው የወንዜው ያ ሸጋው እረኛ
እንዲያው ቀብረር ያለ ጎፈሬው ደገኛ
ከብቶቹን እያየ ሲጫወት ዋሽንቱን
በደስታ ፈዝዤ አየዋለው እሱን

አሆ እማምዬ ደህና ሁን ከተማ
አሆ እማምዬ ተሰነባበተኝ
አሆ እማምዬ ትሰማው የለም ወይ
አሆ እማምዬ ዋሽንቱ ሲጠራኝ
አሆ እማምዬ አንተ ያገሬ ልጅ
አሆ እማምዬ መዋያህ ከማማ
አሆ እማምዬ ወጣው ካንተ ላድር
አሆ እማምዬ ሰለቸኝ ከተማ

ሆ!
ሆ! ...እማምዬ
ሆ!-ሆ!-ሆ!-ሆ!-ሆ! ሆ-ማምዬ!
ሆ! ሆ! ሆ እማምዬ!
ሆ! ሆ! ሆ! እማምዬ!

ደህና ሁን ከተማ ተሰነባብተኝ
ደህና ሁን
ደህና ሁን ከተማ ተሰነባበተኝ
ትሰማው የለም ወይ
ዋሽንቱ ሲጠራኝ

ሆ ማምዬ ሆ ማምዬ
ሆ ማምዬ ሆ ማምዬ
ሆ ማምዬ ሆ ማምዬ
ሆ ማምዬ ሆ ማምዬ
ሆ ማምዬ ሆ ማምዬ
ሆ ማምዬ ሆ ማምዬ
ሆ ማምዬ



Credits
Writer(s): Ejigayehu Shibabaw, Bekel Assefa, Dejene Assefa, Sinke Assefa
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link