Abro Adegay

ችየው ኖሬ ነበር የውስጤን አምቄ
ከእንግዲስ አልችልም ሚስጥሬን ደብቄ
እየዋለ ሲያድር ባሰብኝ ጭንቀቴ
እስቲ መላ በዪኝ እርጂኝ አብሮ አደጌ

የሆድሽን ባላውቅ የዛልሽው በሚስጥር
ጉዳዩን ሳትነግሪኝ ምኑን ልስጥሽ ምክር
አውጥተው ከሰው ጋር ካልተወያዩበት
ውስጥ ውስጡን ይጎዳል ሃሳብና ጭንቀት
እንቅልፍ አሳጥቶ እንዲህ ሚያስጨንቅሽ
ምን ይሆን ሚስጥሩ እስኪ ልጠይቅሽ

ብትነግሪኝስ ፈርቼሽ ነው
በይ አጫውችኝ እረ አይጣል ነው
ምን ገጠመሽ ዱብ እዳ ነው
የምን እዳ ፈተና ነው
ብትነግሪኝስ ፈርቼሽ ነው
በይ አጫውችኝ እረ አይጣል ነው
ምን ገጠመሽ ዱብ እዳ ነው
የምን እዳ ፈተና ነው

አይኔ እየናፈቀው ልቤ እያፈቀረው
አለሁ እስከዛሬ መውደዴን ሳልነግረው
እንደ ምን ልንገረው እኔው አፍ አውጥቼ
የባህል ልማዱን የሴት ወጉን ትቼ

የፍቅር ሃያልነት ሆኖ ሳለ የአቻ
አዲስ ነገር አይደል ሚደርስ ባንቺ ብቻ
ባንድ እጅ አጨብጭቦ
ባንድ በሬ ስቦ
መች ይሆናል ብለሽ አንድ ሰው አስቦ
ምላሹን አይደርስሽ ብቻሽን ብትወጂው
የጋራ ነው ፍቅር ሁሉንም አስረጂው

አታስቢ ፍቅር እኮ ነው
በይ ንገሪው ፈርቼው ነው
አስረጂዋ ምን ልበለው
ምን ይሻላል እረ አይጣል ነው
አታስቢ ፍቅር እኮ ነው
በይ ንገሪው ፈርቼው ነው
አስረጂዋ ምን ልበለው
ምን ይሻላል እረ አይጣል ነው



Credits
Writer(s): Abrishe Zeget
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link