Medafish Ybarek

ጥቂት ልበል ላውራ
ልመስክር እኔም በተራዬ
ባይኖርም ቢቸግርም
ቢጠፋ ቃል
ለውለታሽ ላንቺ እምዬ
በቀጣኝ በገራኝ
ያለስስት ካፍሽ ነጥቆ ባጎረሰኝ
ልጀምር ከሱ አሜን ብለሽ
ይሁን ብለሽ ምርቃቴን ተቀበይኝ
መዳፍሽ ይባረክ
አመድ አፋሽ አያርገው

ዘመንሽ ይለምልም
እድሜሽን ያርዝመው
መዳፍሽ ይባረክ
አመድ አፋሽ አያርገው
ዘመንሽ ይለምልም
እድሜሽን ያርዝመው
ኦኦኦኦኦኦ
ኦኦኦኦኦኦ
አዎ እምዬ
ከአዕምሮ በላይ ነው
ውለታሽ አቻም የለው
ቅኔ ዜማ ቢደረደር
ችሎ የማይገልፀው
የፍቅርን ትርጉም ኖረሽ አሳየሽን
ኑሪልኝ እምዬ ክረሚ
ክፉ አይንካሽ አንቺን
መዳፍሽ ይባረክ
አመድ አፋሽ አያርገው
ዘመንሽ ይለምልም
እድሜሽን ያርዝመው
መዳፍሽ ይባረክ
አመድ አፋሽ አያርገው
ዘመንሽ ይለምልም
እድሜሽን ያርዝመው
ኑሪልኝ ሀሀሀ ኑሪልኝ
ኑሪልኝ ሀሀሀ ኑሪልኝ
ከነ ጉብዝናሽ
ከነ ሙሉ ግርማሽ
ክፉ እንዳይነካሽ
ኑሪልኝ ደምቀሽ
ከነ ጉብዝናሽ
ከነ ሙሉ ግርማሽ
ክፉ እንዳይነካሽ
ኑሪልኝ ደምቀሽ
መዳፍሽ ይባረክ
አመድ አፋሽ አያርገው
ዘመንሽ ይለምልም
እድሜሽን ያኑርሽ ዘለዓለም
መዳፍሽ ይባረክ
አመድ አፋሽ አያርገው
ዘመንሽ ይለምልም
ኦኦ ያኑርሽ ዘለዓለም



Credits
Writer(s): Natnael Yimer
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link