Ye Yared Wub Zema

የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
ምድርና ሰማዩ ታምርሽን ይንገሩ
ፍጥረታት በሙሉ ስላንቺ ይመስክሩ
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ
ድንግል ሆይ እናቴ ከምሳያም የለሽ
ማርያም ድንግል እረዳቴ
የምትደርሽልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ
ተዓምርሽን በዐይኔ አይቻለው
ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለው
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
የእግዚአብሔር ጥበቡ ባንቺ ተገለጠ
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ
የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺ ነሽ
ለፍጥረቱ ሁሉ መሠላል ነሆንሽ
ነገ ባላውቅ እኔንም ቢያስፈራኝ
አንቺ ካለሽኝ በፍጹም አልወድቅም
በፊትሽ እንድታቆም ለምስጋና
ማርያም ልበልሽ በትህተና
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም
ባንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም
አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር
ማርያም ማርያም ይበል ታምርሽን ይናገር
ጨለማው ከፊቴ ተገፈፈ
ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ
ከጎኔ ነይ ስልሽ እጽናናለው
እሳት ገደሉ ሁሉንም አልፈዋለው
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ



Credits
Writer(s): Simone Tsegay
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link