Yemaneh

በመስቀሉ ፡ ገለጠ ፡ የፍቅሩን ፡ ዳርቻ
ልጀነትን ፡ አገኘሁ ፡ በማመኔ ፡ ብቻ
ላልሰሙ ፡ ልንገራቸው ፡ የማን ፡ ነህ ፡ ቢሉኝ
ደም ፡ የተከፈለልኝ ፡ የኢየሱስ ፡ ነኝ

እንድኖር ፡ በኩኔ ፡ በድካሜ ፡ አንገት ፡ እንድደፋ
የጠላቴ ፡ አላማው ፡ ቢሆንለት ፡ እንዳይኖረኝ ፡ ተስፋ
ኢየሱስ ፡ ጠበቃዬ ፡ ቀና ፡ አረገኝ ፡ በደሙ ፡ አንጽቶ
በድል ፡ እራመዳለሁ ፡ ሰንሰለቴ ፡ በኢየሱስ ፡ ተፈትቶ

በወንጌሉ ፡ እውነት ፡ ነጻ ፡ አውጥቶ ፡ ገዝቶኛል ፡ በደሙ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
ፍርድና ፡ ኩነኔ ፡ የሊለበኝ ፡ ገዝቶኛል ፡ በደሙ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
በነጻነት ፡ ልኖር ፡ ነጻ ፡ አውጥቶ ፡ ገዝቶኛል ፡ በደሙ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
ተደላድያለሁ ፡ ሰላሜ ፡ በዝቶ ፡ ገዝቶኛል ፡ በደሙ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
የጌታ ፡ ነኝ ፡ የጌታ ፡ ነኝ ፡ የጌታ ፡ ነኝ ፡ የጌታ ፡ ነኝ

ከሳሼም ፡ መጣ ፡ ሎሴ ፡ ጠርዞ
ማኅተም ፡ አትሞ ፡ ማስረጃውን ፡ ይዞ
ፈራጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ደሙ ፡ ነበረ
ጠላቴም ፡ ሸሸ ፡ እየደነበረ

የማን ፡ ነህ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
የማን ፡ ነህ ፡ የጌታ ፡ ነኝ

በመስቀሉ ፡ ገለጠ ፡ የፍቅሩን ፡ ዳርቻ
ልጀነትን ፡ አገኘሁ ፡ በማመኔ ፡ ብቻ
ላልሰሙ ፡ ልንገራቸው ፡ የማን ፡ ነህ ፡ ቢሉኝ
ደም ፡ የተከፈለልኝ ፡ የኢየሱስ ፡ ነኝ

ክእንግዲህ ፡ ወስኛለሁ ፡ በእርሱ ፡ በቻ ፡ ሕይወቴ ፡ እንዲመካ
ሁሉን ፡ አሸንፋለሁ ፡ የሚረዳኝ ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ወገቤን ፡ ታጥቂያለሁ ፡ በመንፈሱ ፡ ኃይል ፡ ተሞልቼ
ወደፊት ፡ እሄዳለሁ ፡ ያለፈውን ፡ የኋላዬን ፡ ትቼ

በወንጌሉ ፡ እውነት ፡ ነጻ ፡ አውጥቶ ፡ ገዝቶኛል ፡ በደሙ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
ፍርድና ፡ ኩነኔ ፡ የሊለበኝ ፡ ገዝቶኛል ፡ በደሙ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
በነጻነት ፡ ልኖር ፡ ነጻ ፡ አውጥቶ ፡ ገዝቶኛል ፡ በደሙ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
ተደላድያለሁ ፡ ሰላሜ ፡ በዝቶ ፡ ገዝቶኛል ፡ በደሙ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
የጌታ ፡ ነኝ ፡ የጌታ ፡ ነኝ ፡ የጌታ ፡ ነኝ ፡ የጌታ ፡ ነኝ

ከሳሼም ፡ መጣ ፡ ሎሴ ፡ ጠርዞ
ማኅተም ፡ አትሞ ፡ ማስረጃውን ፡ ይዞ
ፈራጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ደሙ ፡ ነበረ
ጠላቴም ፡ ሸሸ ፡ እየደነበረ

የማን ፡ ነህ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
የማን ፡ ነህ ፡ የጌታ ፡ ነኝ

Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Yosef Kassa
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link