Balderesu

ከቀን በአራተኛው በእለተ ሐሙስ
ከወንድሜ ጋራ ስንጋልብ ፈረስ
አልያዘውም ኖሮ ልጓሙን አጥብቆ
አለፈች ህይወቱ ከፈረስ ላይ ወድቆ

እየጠበቀችኝ
እምዬ ከቤት
እንዴት ላረዳት ነው
የወንድሜን ሞት

ባልደራሱ
አልተገራም ወይ ፈረሱ
ባልደራሱ
አልተገራም ወይ ፈረሱ
ባልደራሱ

ምን ብዬ ልንገራት
ምን ብዬ ልንገራት ለእምዬ
ምን ብዬ
ምን ብዬ ልንገራት
ምን ብዬ ልንገራት ለእምዬ
ምን ብዬ
ምን ብዬ ልንገራት
ምን ብዬ ልንገራት ለእምዬ
ምን ብዬ
ምን ብዬ ልንገራት
ምን ብዬ ልንገራት ለእምዬ
ምን ብዬ

ባ ባልደራስ
አልተገራም ወይ ፈረሱ
አልተገራም ወይ ወይ ወይ ወይ
አልተገራም ወይ ወይ ወይ ወይ

አንተ ባልደራስ የፈረስ አባት
ነፍሱን ከገነት ለማታስገባት
ወይኔ ወይኔ
ለናቴ ልጅ ወይኔ ወይኔ
ከሜዳው ነው ወይ ወይ ከፈረሱ
ለሞት ያበቃው ምንድነው እርሱ
ወይኔ ወይኔ
ለናቴ ልጅ ወይኔ ወይኔ
ሳታበጃጀው ልጓም ግላሱን
ያንድ የናቴን ልጅ ነሳኸው ነፍሱን



Credits
Writer(s): Teddy Afro
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link