Alefe Halifu

አለፈ አለፈ
አለፈ አለፈ
አለፈ አለፈ
አቋስሎን አለፈ
አድክሞን አርግፎን አለፈ
የሆነው ቢከብደንም
አልፈናል ግድ የለም አሁንም
የሗላን ወደ ሗላ ጥለን
እንጀምር አብረን ተማምለን
ነጋ ነጋ ነጋ ሌቱ ነጋ በፍቅር ነጋ
ፈካ ፈካ ፈካ ቀኑ ፈካ በፍቅር ፈካ

አኳርፎ ያከረመን አመት
ሊካስ ነው በፍቅር በረከት
አርቆ አነፋፍቆን ከርሞ
ቀን መጣ ሊያወዳጀን ደግሞ
ነጋ ነጋ ነጋ ሌቱ ነጋ በፍቅር ነጋ
ፈካ ፈካ ፈካ ቀኑ ፈካ በፍቅር ፈካ
ለማይጠቅም የማይካስ የነፍስ ዋጋ
ሰው አንከፍልም ቢጠፋም ለሚተካ
እንደ ሞኞች እንደ ከንቱ ክፋይ
ተገፋፍተን መሆን የሞት ሲሳይ
አብሮ መኖር ሲቻል በፍቅር መጠቃቀም
ለምን ጉዳት ሀዘን ዘርቶ እሾህ መልቀም
ከስጋት ይኑር እንጂ ሰላም
ከፍርሀት ፍቅር ይሁን ሰላም

መዋደድ እያለ ቡና መጠራራት
ምነው ከጎረቤት በቀን መፈራራት
አብሮ ማደግ ሲቻል ወደላይ መመንጠቅ
ትርፉ ስጋት ሆኖ ተኳርፎ መጠንቀቅ

ቋንቋውን አጣምሮ አደባልቆ
ምድሩን አሰባስቦ አጠባብቆ
አንዱ ካንዱ ጋር ነው ከፍጥረቱ
መንገዱ እና መውጪያው መግቢያ ቤቱ
ቋንቋውን አጣምሮ አደባልቆ
ምድሩን አሰባስቦ አጠባብቆ
አንዱ ካንዱ ጋር ነው ከፍጥረቱ
መንገዱ እና መውጪያው መግቢያ ቤቱ
አንዱ ካንዱ ጋር ነው ከፍጥረቱ
መንገዱ እና መውጪያው መግቢያ ቤቱ

እስከ መቼ ተነጥላ
ትኑር እናት ልጇን ጥላ
የሰው ሀሳብ ከንቱ ምኞት
አንዱን ሁለት ወገን አርጎት
አልፏል መኖር ተለያይቶ
አጥር ድንበር ጎራ ሰርቶ
ገልጦ ብርሀን ዛሬ ደምቆ
የጋረደን አነፋፍቆ
እስከ መቼ ተነጥላ
ትኑር እናት ልጇን ጥላ
የሰው ሀሳብ ከንቱ ምኞት
አንዱን ሁለት ወገን አርጎት
አልፏል መኖር ተለያይቶ
አጥር ድንበር ጎራ ሰርቶ
ገልጦ ብርሀን ዛሬ ደምቆ
የጋረደን አነፋፍቆ

ነጋ ነጋ ነጋ ሌቱ ነጋ በፍቅር ነጋ
ፈካ ፈካ ፈካ ቀኑ ፈካ በፍቅር ፈካ

ነጋ ነጋ ነጋ ሌቱ ነጋ በፍቅር ነጋ
ፈካ ፈካ ፈካ ቀኑ ፈካ በፍቅር ፈካ



Credits
Writer(s): Elias Melka
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link