Aynih

ዓይንህ ዓይንህ
ዓይንህ ዓይንህ
ኧረ ዓይንህ ኧረ ዓይንህ

ዓይንህ ዓይንህ
ዓይንህ ዓይንህ
ኧረ ዓይንህ ኧረ ዓይንህ
ፈጣሪ ወስኖ ምድርን ከዘረጋት
አንተን የመሰለ መቼ ፈጠረባት
ሱባዔ ገብቼ ለብዙ ዘመናት
ዓይንህን አይቼ ዓይኔን አፈርስኳት
ዓይንህ ዓይንህ
ዓይንህን አሳየኝ በነጋ በጠባ
በልቤ በልቤ
በልቤ እየሰደቅክ የናፍቆት አለንጋ
በሰው በሰው
በሰው እጅ ሹሎ በእግዜር የተሰራ

ዓይንህ ዓይንህ
ኧረ ዓይንህ ኧረ ዓይንህ
ረቂቅ የአብ ስራ

አንተ አንደበተ ርቱ
ሀረግ ነው ተቋምህ

ውብትህም በዝቶ ጠይሞ ቀለምህ
በዝምታህ ሚስጥር
በውበትህ ማህደር
በመውደድህ ወጠመድ ተይዤ ስዳክር
ዓይንህ ዓይኔን ሲያየው
አለው ሚስጥር ጥበብ
ሲመዝን ሲለካ ፍቅርን ሲያገናዝብ
ሰው ወዶ መናፈቅ አርፎ እየተነሳ
ዛሬ ተመልሶ በዓይኔ ተነሳ
ዓይንህ ዓይንህ
ይህ ዓይንህ ወይ ዓይንህ
እንደምን ተሻለኝ
ነፍስ ነፍስ
ነፍስና ስጋዬ ወደውህ ቸገረኝ

የኔ የኔ
የኔ ልብ ከወዴት ያንተስ ወዴት ነው
አሁን አሁን
ሰው ማፍቀር እንደኔ የሚያምርበት ማነው
ላንተ መስተንግዶ የተፈቀደለት
እንዴት ቻለህ ምድሩ የተራመድክበት
አንተን የሚገልጸው አልተገኘም በምድር
ከሰፊው ሰማያት ወይ ካድማስ ባሻገር
ዓይንህ ዓይንህ
ዓይንህን አሳየኝ በነጋ በጠባ
ልቤ ልቤ
በልቤ እየሰደቅክ የናፍቆት አለንጋ
በሰው በሰው

በሰው እጅ ሳይሆን በእግዜር የተሰራ

ዓይንህ ዓይንህ
ኧረ ዓይንህ ኧረ ዓይንህ
ረቂቅ የ አብ ስራ
ሰው ማፍቀር እንደኔ የሚያምርበት ማነው
ዓይንህ ዓይንህ
ኧረ ዓይንህ ኧረ ዓይንህ
ዓይንህ ዓይንህ
ኧረ ዓይንህ ኧረ ዓይንህ
ዓይንህ ዓይንህ
ኧረ ዓይንህ ኧረ ዓይንህ
ዓይንህ ዓይንህ
ኧረ ዓይንህ ኧረ ዓይንህ



Credits
Writer(s): Aster Aweke
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link