Berun Kifetu

ከስም ሁሉ በላይ ኃያል ስም አለው
በዚህ ስም አምነን ድነናል ይኸው
ምስክሮቹ ነን ሕይወት ደርሶናል
ሰማይ ሲጎበኘን ለዓለም በርተናል
ተጠቅልለናል በክርስቶስ በኃያሉ ስም
ከነበርንበት ዓለም የለንም
የሚበልጥ አይተን የሚደንቅ ክብር
ሰውን ኑ እንላለን አልፈን ከምድር
አምላክ ስጋ ሆነ ለኛ ማለደ
ከአብ አስታረቀን ስርየት ወረደ
ሕያው ልጆቹ ነን ዳግም ወልዶናል
ዘላለም ሲያገኘን ከሞት ጠፍተናል
ተጠቅልለናል በክርስቶስ በኃያሉ ስም
ከነበርንበት ዓለም የለንም
የሚበልጥ አይተን የሚደንቅ ፍቅር
ሰው እንጋብዛለን ወደዚህ ክብር
እናንት መኳንንቶች
በሩን ክፈቱ
የክብር ንጉሥ ይግባ
በሩን ክፈቱ
ይሄ ንጉሥ ማነው?
እሱ እግዚአብሔር ነው
የክብር ሁሉ ጌታ?
እሱ እግዚአብሔር ነው
የክብር ሁሉ ጌታ
የክብር ሁሉ ገዢ
እግዚአብሔር ነው
እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኃያል
የሰማይ የምድሩ የልዑላን ጌታ
እግዚአብሔር ነው
እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኃያል
ሆሆ ኃያሉ እግዚአብሔር
እሱ እኛን ጎበኘ
እንድንዘምርለት ዙሪያው ሰበሰበን
ሆሆ እግዚአብሔር ረዳን
እግዚአብሔር አሰበን
በየደረስንበት ኃያል መዝሙር ሆነን
ምስጋና የተገባው እሱ ነው
ውዳሴ የተገባው እሱ ነው
ለኛ ታየን መድኃኔዓለም
እንደሱ የለም ዘለዓለም
ለኛ ተገለጠ መድኃኔዓለም
እንደሱ የለም ዘለዓለም
ዝማሬ የተገባው እሱ ነው
ስግደትም የተገባው እሱ ነው
ለኛ ታየን መድኃኔዓለም
እንደሱ የለም ዘለዓለም
ለኛ ተገለጠ መድኃኔዓለም
እንደሱ የለም ዘለዓለም



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Hanna Tekle, Yerotuletin Yayutal
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link