Ayaremegn

መቼም እኔ አያርመኝ ዛሬም ሰው ወደድኩኝ ልቤን አስረከብኩኝ
ካለፈው ጉዳቴ ሳልማር ቀርቼ ሰጠሁ ለፍቅር እጄን
በል ወዳጄ አድምጠኝ ልንገርህ የልቤን
የአምና የካች አምና የፍቅር ታሪኬን
የእኔ የማፍቀር ጥጉ እስከ ሞት ጫፍ ነበር
አይኔም ልቤም ጭፍን ከወደኩ በፍቅር
ስወድ ሚስጥር የለኝ ለፍቅር የሚሰሰት
ሙሉ ማንነቴን ገላልጬው መሳጠት
እናማ ሲለዩኝ ጉዳቴ ሁለት ነዉ
ዛሬዬን አጥቼ ለነገ እፈራለሁ
ግን አያርመኝ ዛሬም አለሁ ሰው ወድጄ
ለፍቅር ሟች ሆኜነቴ ሰጠሁ እጄን
እንደው ምን ላድርገው ይሄን ልቤን ያሳርፈኝ
ዛሬም ወደድኩ ምኑ አልቀረ ላኮረፈ
ምኙ ልቤ ደግሞ አፈቀረ
መናፈቁን ማሰብ ጀመረ
ካምናው ነገር ዛሬ አልተመከረ
ምኙ ልቤ ደግሞ አፈቀረ (×3)
መቼም እኔ አያርመኝ ዛሬም ሰው ወደድኩኝ ልቤን አስረከብኩኝ
ካለፈው ጉዳቴ ሳልማር ቀርቼ ሰጠሁ ለፍቅር እጄን
ማፍቀሬን አልጠላው ለሰው ሟች መሆኔን
የእኔ ያልኩትን ሰው ከልብ ማመኔን
ስወድም ስወደድ ደስታዬ እንከን የሌው
ስለ ነገ አላስብ ዛሬን ነው ምኖረው
መለየት መኖሩን ሁልጊዜ እየረሳሁ
ደግሜ ደግሜ በፍቅር ወድቄአለሁ
ግን አላስጣለኝም የእኔ ከልብ መውደድ
ፍቅር የሚፀድቀው በሁለት ሲገመድ
ግን አያርመኝ ዛሬም አለሁ ሰው ወድጄ
ለፍቅር ሟች ሆኜነቴ ሰጠሁ እጄን
ምኙ ልቤ ደግሞ አፈቀረ
መናፈቁን ማሰብ ጀመረ
ካምናው ነገር ዛሬ አልተመከረ
ምኙ ልቤ ደግሞ አፈቀረ (×3)



Credits
Writer(s): Yeshi Demelash Unknown
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link