Nanye

ናንዬ ናንዋ
ወርቅ አልማዝ ገላዋ
ከውቤ በርሀ ውለን ከአባ ኮራን
እንደ ተኮላ ወርቅ ከሩቅ እያበራን
እንዋደድ ነበር ሰው ነው ያፈራራን
እንዋደድ ነበር ቀን ነው ያፈራራን

ጣልያን አልጠገነው ባቡሩ ሰባራ
አረማመድ አያውቅ የእኔ እግር ደንባራ
አንቺን ጥሎበት ነው የተጋባው ግራ (ግራ ግራ)
እንዴት ብትናፍቀኝ እንዴትስ ብትወደኝ
እትቱ ስል አይታ ፍቅሯ እየበረደኝ
ከሰው ለምዳ መጣች የባስ ልታነደኝ
ሜሎቲ ቸኮላት ይዤ ባልሄድላት
ነብሱን ይሰጥሻል አራዳ ነው በሏት

ናንዬ (ናንዬ) ናንዋ (ናንዋ)
ወርቅ አልማዝ (ወርቅ አልማዝ) ገላዋ (ገላዋ)
ናንዬ (ናንዬ) ናንዋ (ናንዋ)
ወርቅ አልማዝ (ወርቅ አልማዝ) ገላዋ (ገላዋ)

ከውቤ በርሀ ውለን ከአባ ኮራን
እንደ ተኮላ ወርቅ ከሩቅ እያበራን
እንዋደድ ነበር ሰው ነው ያፈራራን
እንዋደድ ነበር ቀን ነው ያፈራራን

ጎበዝማ ነበር እንዴት ያለ አራዳ
ሸርተት አረገና ጊዜም እንደከዳ
የምቹ መድሃኒት ከደጅሽ እያለ
አይቶ ማሳለፉን ልብሽ እንዴት ቻለ
ሎሚ ተረከዝሽ መሬቱን ሲረግጠው
የኔ ልብ ከወዲህ ምን አስደነገጠው
እንደ አስናቀች ክራር ሳትደረደሪ
ውይ ውይ ሳያስብልሽ ፍቅር እንደሜሪ

ናንዬ (ናንዬ) ናንዋ (ናንዋ)
ወርቅ አልማዝ (ወርቅ አልማዝ) ገላዋ (ገላዋ)
ናንዬ (ናንዬ) ናንዋ (ናንዋ)
ወርቅ አልማዝ (ወርቅ አልማዝ) ገላዋ

ከውቤ በርሀ ውለን ከአባ ኮራን
እንደ ተኮላ ወርቅ ከሩቅ እያበራን
እንዋደድ ነበር ሰው ነው ያፈራራን
እንዋደድ ነበር ቀን ነው ያፈራራን



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Lij Michael
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link