Leman Lemash

ለማን ልማሽ እኔ አንቺን ፍቅሬ
ብዙ ነው ሚስጥሬ
ቢከፋኝም ሆዴን ቢበሰው
አላማሽም ለሰው
ለማን ልማሽ እኔ አንቺን ፍቅሬ
ብዙ ነው ሚስጥሬ
ቢከፋኝም ሆዴን ቢበሰው
አላማሽም ለሰው

አያጣዉምና ፍቅርን እንቅፋት
ከፍቶኝ ብቀየምሽ ባንድ ቀን ጥፋት
መልሼ ልፀፀት እራሴን ልከሰው
እንዴት አሳልፌ አንቺን ልማሽ ለሰው

ለማን ልማሽ እኔ አንቺን ፍቅሬ
ብዙ ነው ሚስጥሬ
ቢከፋኝም ሆዴን ቢበሰው
አላማሽም ለሰው

ዞሮ መግጠም ላይቀር አንድ ቀን
ምንድነው ሐሜት
ብዙ ያሳያል ማን እንደጊዜ
እንደመሰንበት
በሚወዱት አያምርም ሐሜት
ለሰሚም አይበጅ
ትርፍ የለዉም የራስ ሰው ቢያሙት
ያስገምታል አንጂ

ኧረ እኔስ ለማን ልማሽ
ኧረ እኔስ ለማን
አይሆንለት ሆዴ አንቺን ርቆ
መቻል ያውቃል ማሳለፍ ስቆ
አይሆንለት ሆዴ አንቺን ርቆ
መቻል ያውቃል ማሳለፍ ስቆ

ዉ ዉሁሁ ኦሆሆሆሆ
ዉ ዉሁሁ ኦሆሆሆሆ

ለማን ልማሽ እኔ አንቺን ፍቅሬ
ብዙ ነው ሚስጥሬ
ቢከፋኝም ሆዴን ቢበሰው
አላማሽም ለሰው

ለማን ልማሽ እኔ አንቺን ፍቅሬ
ብዙ ነው ሚስጥሬ
ቢከፋኝም ሆዴን ቢበሰው
አላማሽም ለሰው

ቢኖርም ቅሬታ ችሎ ማለፍ እንጂ
የወዳጅ ገመና አይዘራም ደጅ
ወድሻለሁና ያንቺ በኔ ይቅር
በወሬ አይፈታም እውነተኛ ፍቅር

ለማን ልማሽ እኔ አንቺን ፍቅሬ
ብዙ ነው ሚስጥሬ
ቢከፋኝም ሆዴን ቢበሰው
አላማሽም ለሰው

ዞሮ መግጠም ላይቀር አንድ ቀን
ምንድነው ሐሜት
ብዙ ያሳያል ማን እንደጊዜ
እንደመሰንበቱ
በሚወዱት አያምርም ሐሜት
ለሰሚም አይበጅ
ትርፍ የለዉም የራስ ሰው ቢያሙት
ያስገምታል እንጂ

ኧረ እኔስ ለማን ልማሽ
ኧረ እኔስ ለማን
አይሆንለት ሆዴ አንቺን ርቆ
መቻል ያውቃል ማሳለፍ ስቆ
አይሆንለት ሆዴ አንቺን ርቆ
መቻል ያውቃል ማሳለፍ ስቆ



Credits
Writer(s): Teddy Afro
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link