Tilik New

ከደመና ከሰማይ
ከዓመታት ከፍጥረት በላይ
ከጊዜ ገደብ ከሁኔታ
የሚልቅ ከአዕምሮ እይታ

እውቀቱ ማይመረመር
ችሎታው ማይደረስበት
የዘመናት ንጉስ እግዚአብሔር

በስፍራ የማይወሰን
በዓመታት የማይቆጠር
ስልጣናት አለቅነት
የተሞላ የሁሉ አባት

ነፋሳቱ ባህሩ
ተራሮች ወንዞቹ
ይሰግዱለታል የእጆቹ ሥራ ሁሉ

ትልቅ ነው እግዚአብሔር
ከሀሳቤ በላይ
ትልቅ ነው እግዚአብሔር
ቃላት የማይገልጹት



Credits
Writer(s): Exodus Getahun
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link