Helina

ብወድቅ እነሳለው አልቀርም ወድቄ
ባጣም አገኛለሁ ከሆነ እድሌ
ዛሬም ያልፍ እና በነገ ይተካል
የማታልፍ ነፍስን ግን ማን ይገዛታል

ቀስ በቀስ እጏዛለሁ
አንድ ቀን እደርሳለው

ለሁሉም ዘመን አለው እርስም በርሱ ይተካካል
ዘሬ የሚታየው ነገ ደግሞ ይጠፋል
ነፋስን ተከትሎ ከንቱ እራሱን ያጣል
የሰው ልጅን ኑር ሲለው ግን ከህሊናው ታስሯል

የዓለምን ዙረት የቱ ሰው አቁሟል
ከተፃፈለት እድል ማንስ ያመልጣል
የሚሆነውም የማይሆነውም ተራውን ይጠብቃል
ለማይጨበትስ ጉም መቼ ልብ ይጣላል

ቀስ በቀስ እጏዛለሁ
አንድ ቀን እደርሳለው

ለሁሉም ዘመን አለው እርስም በርሱ ይተካካል
ዘሬ የሚታየው ነገ ደግሞ ይጠፋል
ነፋስን ተከትሎ ከንቱ እራሱን ያጣል
የሰው ልጅን ኑር ሲለው ግን ከህሊናው ታስሯል

ለሁሉም ዘመን አለው እርስም በርሱ ይተካካል
ዘሬ የሚታየው ነገ ደግሞ ይጠፋል
ነፋስን ተከትሎ ከንቱ እራሱን ያጣል
የሰው ልጅን ኑር ሲለው ግን ከህሊናው ታስሯል

ለሁሉም ዘመን አለው እርስም በርሱ ይተካካል
ዘሬ የሚታየው ነገ ደግሞ ይጠፋል
ነፋስን ተከትሎ ከንቱ እራሱን ያጣል
የሰው ልጅን ኑር ሲለው ግን ከህሊናው ታስሯል



Credits
Writer(s): Dawit Cherent
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link