Kanchiga New

ሰማይ እያስነካሽ እየጣልሽው መሬት
ልጓም ሆነሽበት አቤት ልቤ ይሂድ ወዴት
አንድ ጊዜ ወደዚ ፈገግ አንዴ ደሞ ወደዛ
አልማዝ እያስነካሽ ጉጉ ልብሽ ፍቅሬን ገዛ
ጨወታው ሊቀየር ድንገት ከታች ሆኖ ወደላይ
ዋስትና የለኝም እኔ ዛሬ እንጂ ነገ ላይ
አንቺ ካለሽ ለኔ ዉዴ እኔም ላንቺ ካለው
ምን እንጠብቃለን ታዲያ ማበድ መደሰት ነው

ካንቺ ጋር ነው ፍቅር ጨዋታ ካንቺ ጋር ነው (አንቺን ሳገኝ ነው)
ካንቺ ጋር ነው ዛሬ ደስታ ካንቺ ጋር ነው (በይ ያዥ እና ምሪኝ)
ካንቺ ጋር ነው ፍቅር ጨዋታ ካንቺ ጋር ነው (ፍቅር ይፈልጋል)
ካንቺ ጋር ነው ዛሬ ደስታ ካንቺ ጋር ነው (አንቺን አግኝቷል)

ደስታ ልቤን ሞልቶት ፍቅር ሀሴት የማደርገው
በራሪዋን ኮከብ አይኔን አንቺን ሳገኝ ነው
አትንፈጊኝ ብርሀን ሰተሽ ካሰብኩት አድርሺኝ
ፍቅር አውሮኛል ይኸው በይ ያዥ እና ምሪኝ
ስዕሉ ከታየሽ ውዴ የምለው ግልፅ ነው
ይሄን ተጓዥ ልቤን ድንገት ፍቅርሽ ነው ያቆመው
ይዞራል ይዞራል ፍቅር ይፈልጋል
ዞሮ ዞሮ ልቤ አረፈ ዛሬ አንቺን አግኝቷል

ካንቺ ጋር ነው ፍቅር ጨዋታ ካንቺ ጋር ነው (አንቺን ሳገኝ ነው)
ካንቺ ጋር ነው ዛሬ ደስታ ካንቺ ጋር ነው (በይ ያዥ እና ምሪኝ)
ካንቺ ጋር ነው ፍቅር ጨዋታ ካንቺ ጋር ነው (ፍቅር ይፈልጋል)
ካንቺ ጋር ነው ዛሬ ደስታ ካንቺ ጋር ነው (አንቺን አግኝቷል)

አራዳ ግልፅ ነው አቤት አውነቱን ንገራት
ሳይጠየቅ አይመለስ ክፈት ልብህን አሳያት
ተረጂው አለም ዘጠኝ ዛሬ አንዱን ያዥው
ገንዘብ አላቂ ጠፊ ነው ፍቅርን ምረጭው
አለሽ አንድ ነገር ልብ የሚሰርቅ አፍዞ የሚያስቀር
አስገራሚው ሁለመናሽ ነፃነትሽ ሲያምር
ለካ እንደዚ እብድ ነሽ ቆንጆ መቀነትሽ የታል
ፈተሸዋል ለካ አሁን ፍቅር ፈልገሻል

ካንቺ ጋር ነው ፍቅር ጨዋታ ካንቺ ጋር ነው (አንቺን ሳገኝ ነው)
ካንቺ ጋር ነው ዛሬ ደስታ ካንቺ ጋር ነው (በይ ያዥ እና ምሪኝ)
ካንቺ ጋር ነው ፍቅር ጨዋታ ካንቺ ጋር ነው (ፍቅር ይፈልጋል)
ካንቺ ጋር ነው ዛሬ ደስታ ካንቺ ጋር ነው (አንቺን አግኝቷል)



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Samuel Teferi
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link