Enja

እህህ እህህ
ሰው እህህ ካለ
ተርጥሩ እዚ ቦታ
አንድ ነገር አለ
እንጃ ምን አንደሆንኩ ያስነካሽኝን
ካገር ከሞላ ሰው የምለው አንቺን
እንጃ ምን አንደሆንኩ እኔስ ምን አውቄ
መወሰዴ በዛ ባንቺ መነጠቄ
እንዲያው ምን ይሆን

እንደ ፈሪ ዱላ ባልጠበኩት አፍታ
ድንገት አገኘኝ ወይ ፍቅርሽ አጉል ቦታ
እንጃ ምን አንደሆንኩ ያስነካሽኝን
ካገር ከሞላ ሰው የምለው አንቺን
አንጃ ምን አንደሆንኩ እኔስ ምን አውቄ
መወሰዴ በዛ ባንቺ መነጠቄ
እንድያው ምን ይሆን

ልጏዝ እንጂ ደሜ ነፍሴን
አልሆንኩም ዘንድሮስ እራሴን
ልክ አጣሁኝ ስወድሽ
ምኔን ነው የነካው ምንሽ

አውቃለው ነክቼ የርግብ ላባ ስሱን
ግን እንዳንቺ ገላ እንጃ መለስለሱን
አስር አይነት ቆንጆ የሚሰራ መልክ
ብቻሽን አድሎ እኔ ምን ላድርግ
እንጃ

ቆንጅቷ ወርቀ ሰብ
አንጥሮ የሰራሽ በጥበብ
አለቀ ደቀቀ ልቤ እጣው ከውበት ወደቀ
አጣሁኝ መዳኛ
ምን አይነት ፍቅር ነው ሀይለኛ
ዘንድሮስ እዳዬ እህህ ብቻ ነው ዜማዬ

እንጃ ምን አንደሆንኩ ያስነካሽኝን
ካገር ከሞላ ሰው የምለው አንቺን
እንጃ ምን አንደሆንኩ እኔስ ምን አውቄ
መወሰዴ በዛ ባንቺ መነጠቄ
እንጃ ምን አንደሆንኩ ያስነካሽኝን
ካገር ከሞላ ሰው የምለው አንቺን
እንጃ ምን እንደሆንኩ እኔስ ምን አውቄ
መወሰዴ በዛ ባንቺ መነጠቄ
እንጃ ምን አንደሆንኩ



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Natinael Girmachew
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link