Bihon

ስሚኝ አጠፋ በደልክ ያልሺኝ ሰው
አታወሪኝ ምነው
ዛሬም በተስፋ ጠብቅሻለሁ
እናውጋ! እላለው
ጠዋት ማታ 'ማትቀሪ ደጁ
ነጠላሽ ከልብሽ ንጹሕ
ምሕረት ከራስ ይጀምራል (ስሚኝ)
ያን ጊዜ ፈጣሪ ይሰማል
ከቤቱ መሄድ ይቆይሽ
ይቅር በይ ቅድሚያ ከቤትሽ
ሁሌ ስትሄጂ አይሻለሁ ዓለም
ሰላምሽ ግን በዳይሽ ጋር ነው

ቢሆን!
ቦታ ብትሰጪኝ ላፍታ ብታዳምጪኝ
ቢሆን!
ልብሽ ከልቤ ሰላም ነበርን
አንቺ እና እኔ!

ኤይ... ኤይ
ፀሐይ ማልዳ ብትወጣም
ኤይ... ኤይ
ያለ ይቅርታ አልነጋም
ኤይ... ኤይ
ምሕረትን ነፍጎ ያደረ
ኤይ... ኢ... ኤይ
በጨለማ ዋለ!!!
(ኤይ... ኤይ)
ቢሆን!
(ኤይ... ኤይ)
(ቦታ ብትሰጪኝ...!)
(ኤይ... ኤይ)
በጨለማ ዋለ!!!

"ቶ" መስቀልሽ ግንባርሽ ላይ የተነቀስሽበት
ምነው አያቅፈኝ ከሰው አነስኩበት?
በቃል ብትረቺኝ ብወድቅልሽ ያገኘ አጌጠበት
ቅኔ አማርኛሽ ወርቅ በዝቶበት
ዘንግተን ቃሉን ማሕተቡን ብናስረው ምንድነው?
ተይ አፍሮ ይገባል ፍቅር የሌለው
ማውጋት ይበጃል በአክሱም መስቀሌ እምልልሻለሁ
ምሕላውን ተይ አጠገብሽ ሳለሁ!!!

ቢሆን!
ቦታ ብትሰጪኝ ላፍታ ብታዳምጪኝ
ቢሆን!
ልብሽ ከልቤ ሰላም ነበርን
አንቺ እና እኔ!

ኤይ... ኤይ
እግር ያደርሳል ከቤቱ ግንብ
ኤይ... ኤይ
ይቅርታ ግን ከልብ
ኤይ... ኤይ
መቅደስ ሰው በእጁ ከሰራው
ኤይ... ኤይ
የእርሱ ጥበብ ገላው
ኤይ... ኤይ
ፀሐይ ማልዳ ብትወጣልሽ
ኤይ... ኤይ
አልነጋም ስልሽ
ኤይ... ኤይ
ምሕረትን ነፍጎ ያደረ
ኤይ... ኢ... ኤይ
በጨለማ ዋለ!!!

ቢሆን!
(ኤይ... ኤይ)
(ቦታ ብትሰጪኝ...!)
(ኤይ... ኤይ)
ቢሆን!
በጨለማ ዋለ!!!

(ኤይያ... ኤይያ... ኤይያ)
(ቦታ ብትሰጪኝ...!)
(ኤይያ... ኤይያ... ኤይያ)

ነጠላሽ የዋህ በውኃ ይነጣል
ልብሽ ግን ይቅርታ እንዴት ያጣል?
ላጠፋ ሰው ምሕረት አሻፈረኝ ብለሽ
የለበስሽው ሸማ በለጠሽ
አምላክ የሰጠውን መች ከሰው ወሰደው?
ሰላምን በዳይ ጋር አስቀመጠው
ጥበቡ ጠብ ሲል ከባሕር ይጠልቃል
አንድ ይቅርታ ለዓለም ይበቃል

ቢሆን!!!



Credits
Writer(s): Rophnan, Jorga Mesfin
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link