Atteykwat

አትጠይቋት ምክንያቷን
ሰበብ አያጣም ቀን ሲደምር
ብዬ እንኳን ጊዜን ማመን ቸገረኝ
ላንድ እኔው መታ መልስ እያጠረኝ
በመውደድ ሚዛን በደል ሲለካ
በአይን ያዩት ሀቅ ውሸት ለካ
በቃ አውቃው እንጂ ጨክና በኔ
አታረግም አኩያየው ባይኔ
ከፍቅር አንፃር በደል ሲለካ
መርዝ ያሉት ሀቅ ይረክሳል ለካ(አው)
በቃል ያሰርነው በቀን ከላላ
ሆድ ይፍጀው እንጂ ምንሊባል ሌላ
ይብላኝ በይልኝ አለም ብትረሳሽ
ፍቅር ለማነሳሽ
ይብላኝ ነው እንጂ ላልፈታው ህልሜን
ሆድ ይፍጀው ህመሜን(ይብላኝ)
ይብላኝ በይልኝ አለም ብትረሳሽ
ፍቅር ለማነሳሽ
ይብላኝ ነው እንጂ ላልፈታው ህልሜን
ሆድ ይፍጀው ህመሜን(ይብላኝ)

አትጠይቋት ምክንያቷን
ሰበብ አያጣም ቀን ሲደምር
ብዬ እንኳን ጊዜን ማመን ቸገረኝ
ላንድ እኔው መታ መልስ እያጠረኝ
መቻሉ ሳያንስይቅር መለቱ
ፀፀት ነው በሰው አፍ መግባቱ
ባይገባውም መከፋት ጎኔ
መልካምነትሽ ሀይል ነው ለኔ
ወትሮም ዞር ነው የሚለው ከርሞ
የዚች አለም ፍርድ አያውቅም ቆሞ(አው)
ከፊት ያመኑት ሲጥል ከኋላ
ሆድ ይፍጀው እንጂ ምን ሊባል ሌላ
ይብላኝ ነው እንጂ ላልፈታው ህልሜን
ሆድ ይፍጀው ህመሜን(ይብላኝ)
ይብላኝ በይልኝ አለም ብትረሳሽ
ፍቅር ለማነሳሽ
ይብላኝ ነው እንጂ ላልፈታው ህልሜን
ሆድ ይፍጀው ህመሜን(ይብላኝ)



Credits
Writer(s): Samuel Alemu, Bisrat Surafel
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link