ለማለት አብቃኝ Lemalet Abkagne

አምላኩን እንዳመነ እንደ እዮብ እጸናለሁ
መከራን ታግሼ ድል ነሳለሁ
ያዩኝ ሲሳለቁ እምነቴን አጣጥለው
አያድን አምላክህን ተወው
ስደበውና ሙት እርገመው
ቢሉኝ አንተን አልበድል አልተው

ራቁቴን ከእናቴ ማህጸን ወጥቻለሁ
ራቁቴንም ወደምድር አፈር እመለሳለሁ
እግዚአብሔር ሰጠኝ እግዚአብሔር ነሳኝ
ስሙ ይክበር ለማለት አብቃኝ
እግዚአብሔር ሰጠኝ እግዚአብሔር ነሳኝ
ስሙ ይክበር ለማለት አብቃኝ

የምድርን በረከት ለኔ አብዝተህልኝ
ቸርነት አድርገህ ጎበኘኧኝ
በፍቅር ላካፍል እንዲበዛ በረከት
ላግዝ ወንድሜን ሳልሰስት
ሀብት አላፍቅር ካንተ እንዳይለየኝ
አንተን መከተል እንዳያግደኝ

ራቁቴን ከእናቴ ማህጸን ወጥቻለሁ
ራቁቴንም ወደምድር አፈር እመለሳለሁ
እግዚአብሔር ሰጠኝ እግዚአብሔር ነሳኝ
ስሙ ይክበር ለማለት አብቃኝ
እግዚአብሔር ሰጠኝ እግዚአብሔር ነሳኝ
ስሙ ይክበር ለማለት አብቃኝ

የኑሮ ቀዳዳ በዝቶ ችግር ቢሰፋ
ረዳቴ ኢየሱስ ነህ የኔ ተስፋ
አንተ እስክትጎበኘኝ ችግሩ ቢሰፋ
ፈታኙ ቢያቀርብ ጉቦ ሙስና
እቆማልሁ ለፍትህ አልደለልም
ከጣፋጭ ፍቅርህ ከቶ አልለይም

ራቁቴን ከእናቴ ማህጸን ወጥቻለሁ
ራቁቴንም ወደምድር አፈር እመለሳለሁ
እግዚአብሔር ሰጠኝ እግዚአብሔር ነሳኝ
ስሙ ይክበር ለማለት አብቃኝ
እግዚአብሔር ሰጠኝ እግዚአብሔር ነሳኝ
ስሙ ይክበር ለማለት አብቃኝ



Credits
Writer(s): Yilma Asrat
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link