Alena

ገና ከጅምር ሰናይ ሰናዩን
ያውቀው የለም ወይ ልብሽ ጉዳዩን
ፍቅርሽን ላልተው አቃተኝ ብዬ
ምኔን ልስጥሽ ምኔን ከልክዬ
ከነብነብ አርጊኝ በይ በነጠላሽ
መውደድ እኮ ነው የመውደድ ምላሽ
ገና ነው ገና አለን አለና
መዋደዳችን መች ተነካና
ፍቅርሽን ላልተው አቃተኝ ብዬ
ምኔን ልስጥሽ ምኔን ከልክዬ
ሳይጠበን የቤቱ ስፋት
ትናንት ያገኘን እንቅፋት
ዛሬም ላይ መጣ ዳግመኛ
ተው ያሉሽን ስለኛ
እንኳንም በዚች ጸሀይ
ያኔም ባመሻሽ ፍቅር ላይ
ወረት ከቤቱ ሳይገባ
ስንቱን አልፈናል በላምባ
ሲፈትን ቀን እያዞረ
ቃሉን አክብሮ ለኖረ
አይቀርም አንጀት ያርሳል
ጊዜም የልብን ያደርሳል
የፍቅር ካባ መልበሱ
ሲያምርብን ግርማ ሞገሱ
አይተሸል እና የኔ አለም
ከኔ የሚለይሽ የለም
አውቃለው አምናለው
ያንቺ ቃል የኔም ነው
ቀን አብሮ ማታ አብሮ
ያኑረን አፋቅሮ
የማይመስል ነገር
የማይመስል ነገር
አትፍሪ ስለኛ ቢወራ ቢነገር
እስካለው በምድር ላይ
እስካለሽ በአለም ላይ
አውቃለው ታውቂያለሽ እንደማንለያይ
ገና ገና ገና አለ ገና
ገና አለ ገና
ትናንትም ዛሬም ፍቅር ነውና
ገና ገና ገና አለ ገና
ገና አለ ገና
የማይመስል ነገር
የማይመስል ነገር
አትፍሪ ስለኛ ቢወራ ቢነገር
እስካለው በምድር ላይ
እስካለሽ በአለም ላይ
አውቃለው ታውቂያለሽ እንደማንለያይ
ገና ገና ገና አለ ገና
ገና አለ ገና
ትናንትም ዛሬም ፍቅር ነውና
ገና ገና ገና አለ ገና
ገና አለ ገና



Credits
Writer(s): Charlie Everley Ryder, Joshua Paul Burgess, Kimberley Michelle Pflaum
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link