Chapter 4 : Tineshua Jelba

ሰባራ ህልም አለችኝ ልፋት የሰበራት
ነፋስ ማዕበሉ ውሃው ሲያንገላታት
ተጥላ እንዳትቀር መልሼ አዋቀርኳት
ደግማ እንዳታፈስ በቅጥራን ለበጥኳት

አሻግሬ እያየው ጀልባዬን ጠገንኳት
ታደርስ ይሆን ብዬ ብዙ ለፋሁባት

ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ
ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ
ትንሿ ጀልባዬ

ድካሙ ብጫነኝ ስራዬን እንዳልቀጥል
ዋርካው ስር አሸለብኩ ወገቤን ላሳርፍ
ትንሽ እንደቆየ የምስራቅ ነፋስ መጥቶ
ጀልባዬን ወሰዳት በወንዙ ታግዞ

ውሃው ቢያንሳፍፋት ስቃ ጥላኝ ሄደች
በአውራቂሱ ነፋስ እየተደሰተች

ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ
ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ
ትንሿ ጀልባዬ

በከንቱ ደከምኩኝ ምንም ላትፈይድ
ጊዜዬን ፈጀሁት የትም ለማትደርስ
ቁጭት ከንዴት ጋር ተባብረው ቢያፍኑኝ
ከሚታየኝ ቅዠት ድንገት አባነኑኝ

ዓይኔን ከሰመመን ታግዬ ብገልጥ
ጀልባዬን አየሗት ወንዙን ስትታገል
ነፋስ ቢደልላት ይዟት ሊኮበልል
"አልሄድም" አለችው ጥላኝ ላትሻገር

ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ
ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ
ትንሿ ጀልባዬ



Credits
Writer(s): Dawit Cherent
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link