Yehuna (Interlude)

ባልገባኝም ብርሃን ፈገግ ብል
ሳቄን ማን ወሰደው እስከምል
ድምፅ የለም ባዶ ነው ኃላዬ
ምላስ ጣቴ ሆኖ በትር ነው ዝናዬ

ጉድጓድ እና ዝናብ ኩሬን ቢደግሱ
ተስካር ከእኔ ቤት ነው ንፍሮ ነው ከእነሱ

ይሁና እምዬ ልፈተን
ሁሉም ከፍቶት ያውቃል አንድ ቀን
አልቀመጥ አለኝ የደስታ አክሊል
ልቤም አልፀና አለ ዝም ሲል

ይሁና እምዬ ልፈተን (ልፈተን)
ሁሉም ከፍቶት ያውቃል አንድ ቀን (አንድ ቀን)
አልቀመጥ አለኝ የደስታ አክሊል (የደስታ አክሊል)
ልቤም አልፀና አለ ዝም ሲል

ዝም ሲል፣ ዝም ሲል
ኦ ኦ
ዝም ሲል፣ ዝም ሲል



Credits
Writer(s): Mikiyas Mengistu Beyene
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link