And Qal

የጸና መሠረት የከበረ ፍቅር
ካንደበቴ ሳይኾን ከዝምታዬ ሥር
ያው ተጽፎልሻል ከዓይኖቼ መኻል
የፍቅር አበባ የመውደዴ ስዕል

አንድ ቃል
እባክሽ አንድ ቃል
አውቃለኹኝ በይኝ ማወቅሽ ይበቃል
ከምን ላውራ ፍርኃት እሚያስጥለኝ
ከመርበትበት ዝናብ የሚገላግለኝ
አንድ ቃል
እባክሽ አንድ ቃል
አንድ ቃል
እባክሽ አንድ ቃል

እኔ ሱፍ አበባ አንቺ የኔ ፀሐይ
በዞርሽበት ኹሉ እየዞርኩ እምታይ
አውቃለኹኝ በዪኝ ፍቅርሽ ልቤን ይጥራ
መውደዴን ሰው ይወቅ ምንም ሳላወራ

አንድ ቃል
እባክሽ አንድ ቃል
አውቃለኹኝ በይኝ ማወቅሽ ይበቃል
ከምን ላውራ ፍርኃት እሚያስጥለኝ
ከመርበትበት ዝናብ የሚገላግለኝ
አንድ ቃል
እባክሽ አንድ ቃል
አንድ ቃል
እባክሽ አንድ ቃል

እስኪ ልጠይቅሽ በነፋሳት ጩኸት
በምንወደው ሰማይ በደመናው ጥለት

እስኪ ልጠይቅሽ በፀሐይዋ ድምቀት
ባገርሽ ባንዲራ በማርያም መቀነት

አንድ ቃል
እባክሽ አንድ ቃል
አውቃለኹኝ በይኝ ማወቅሽ ይበቃል
ከምን ላውራ ፍርኃት እሚያስጥለኝ
ከመርበትበት ዝናብ የሚገላግለኝ
አንድ ቃል
እባክሽ አንድ ቃል
አንድ ቃል
እባክሽ አንድ ቃል



Credits
Writer(s): Solomon Sahele, Michael Belayneh
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link