Sdet

አሀሀሀሀ
ስለፍቅር ሲባል ስለ ፀብ ካወራን ተሳስተናል
አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል
አጥተናል እውነት ነው ተቸግረን ብዙ አይተናል
የመጣነው መንገድ ያሳዝናል
እግር ይዞ እንዴት አይሄድም
ሰው ወደፊት አይራመድም
አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ
ለምን ይሆን የራበው ሆዴ
ብራናው ይነበብ ተዘርግቶ በአትሮነሱ ላይ
የነ ፋሲለደስ የነ ተዋናይ
የት ጋር እንደሆን ይታይ የኛ ጥበብ መሠረቱ
የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ
ሳይራመድ በታሪክ ምንጣፍ
ሰው አይደርስም ከዛሬ ደጃፍ
አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ
ለምን ይሆን የራበው ሆዴ
ከአድማስ እየራቀ
ምነው ይሄ መንገድ ያባክነኛል
በየት በኩል ብሄድ
ወደ እረፍት ሀገሬ ቶሎ ያደርሰኛል
ቀስተዳመና ነው
የለበስኩት ጥበብ የያስኩት አርማ
አልጠላም ወድጄ
የነፍሴ ላይ ፋኖስ እንዲያይ ጨለማ
አንተ አብርሃም የኦሪት ስብሃት
የነ እስማኤል የይስሃቅ አባት
ልክ እንደ አክሱም ራስ
ቀርፀሃት ራሴን
በፍቅር ጧፍ ለኩሳት ነፍሴን
ግን አትዛል ቀና ሁን ልቤ
የህልሜን ከነዓን እንዳይ ቀርቤ
ሰው ለመውደድ ካልኩኝ ደከመኝ
ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ
አመመኝ አመመኝ
እኔን አመመኝ
አመመኝ አመመኝ
እኔን አመመኝ
ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ
ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ
እኔን አመመኝ እኔን አመመኝ
እኔን አመመኝ እኔን
አሀሀሀሀ
ስለፍቅር ሲባል ስለ ፀብ ካወራን ተሳስተናል
አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል
አጥተናል እውነት ነው ተቸግረን ብዙ አይተናል
የመጣነው መንገድ ያሳዝናል
እግር ይዞ እንዴት አይሄድም
ሰው ወደፊት አይራመድም
አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ
ለምን ይሆን የራበው ሆዴ
የኦርዮን ኮኮብ
የሩቅ ሰማይ መንገድ የሌት በራሪ
የልቤን አርጋኖን
በደመናው መስኮት ዘልቀሽ ንገሪ
ቀስተዳመና ነው
የለበስኩት ጥበብ የያስኩት አርማ
አልጠላም ወድጄ
የነፍሴ ላይ ፋኖስ እንዲያይ ጨለማ
አንተ አብርሃም የኦሪት ስብሃት
የነ እስማኤል የይስሃቅ አባት
ልክ እንደ አክሱም ራስ
ቀርፀሃት ራሴን
በፍቅር ጧፍ ለኩሳት ነፍሴን
ግን አትዛል ቀና ሁን ልቤ
የህልሜን ከነዓን እንዳይ ቀርቤ
ሰው ለመውደድ ካልኩኝ ደከመኝ
ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ
አመመኝ አመመኝ
እኔን አመመኝ
አመመኝ አመመኝ
እኔን አመመኝ
ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ
ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ
እኔን አመመኝ እኔን አመመኝ
እኔን አመመኝ እኔን
አሀሀሀሀ



Credits
Writer(s): Teddy
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link