Mamayie

ከረጅም ማማ ላይ ጥንቅሽ የበላ ሰው
ከጎድጓዳ ስፍራ ጠይም የሳመ ሰው
እንኳን ሽማግሌ ዳኛም አይመልሰው
እንኳን ሽማግሌ ዳኛም አይመልሰው
ደጅ ፀናው ደጅ ጠናው ከእንግዲህስ ታከተኝ
የሆዷን ጠይቆ ማን ባሰናበተኝ
ደጅ ፀናው ደጅ ጠናው ከእንግዲህስ ታከተኝ
የሆዷን ጠይቆ ማን ባሰናበተኝ

አጋሙን ግራሩን ጎዝጉዘው ቢተኙ
መች ይጎረብጣል የልብን ካገኙ
ቁጣዋ ባልነበር ያ መነጫነጯ
የውሃ ዳር ሎሚ ነው የሚመስለው ጉንጯ
ደጅ ፀናው ደጅ ጠናው ከእንግዲህስ ታከተኝ
የሆዷን ጠይቆ ማን ባሰናበተኝ
ደጅ ፀናው ደጅ ጠናው ከእንግዲህስ ታከተኝ
የሆዷን ጠይቆ ማን ባሰናበተኝ

ማማዬ ማማዬ ኸረ ነይ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ ሸጋ ልጅ ማማዬ

ማማዬ ማማዬ ኸረ ነይ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ

አይነ ኮሎ ሽንጠ ሎጋ የወለዱ እንደሆን
መልካም ፀባይ ያላት የወለዱ እንደሆን
እውቀት የምትሻ የወለዱ እንደሆን
ታመጣለች አማች ብረት መዝጊያ የሚሆን

ማማዬ ማማዬ ኸረ ነይ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ ሸጋ ልጅ ማማዬ
መልኬ ብቻ በቃኝ የሆነች እንደሆን
ጥሩ ኑሮ በጥባጭ የሆነች እንደሆን
እንኳንስ ለባሏ ለእናቷም አትሆን
እንኳንስ ለባሏ ለእናቷም አትሆን
ማማዬ ማማዬ ኸረ ነይ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ ኸረ ነይ ማማዬ
ካገቡ እንኳን አይቀር ሸጋ መልካም ቆንጆ መርጠው ያገባሉ
ካፈቀሩም አይቀር እውቀት የምትሻ መርጠው ያፈቅራሉ
ከወደዱም አይቀር መልካም ፀባይ ያለት መርጠው ያገባሉ
ገንዘብ አላት ብሎ መልከ ጥፉ ማግባት
ገንዘቡም ያልቅ እና ሁለተኛው ጥፋት
ገንዘቡም ያልቅ እና ሁለተኛው ጥፋት
መች ይቀርላታል ካልተጠነቀቀች
ካልተጠነቀቀች መች ይቀርላታል
ካልተጠነቀቀች መች ይቀርላታል

አንድ ቀን ቀልጣፎች ባሏን ይነጥቋታል
አንድ ቀን ቀልጣፎች ባሏን ይነጥቋታል
በቴስታ በዱላ የሚማታ ከሆን
በሆነው ባልሆነው የሚቀና ከሆን
የት ወጣሽ የት ገባሽ የሚያበዛ ከሆን
እንኳን ብረት መዝጊያ የጭራሮም አይሆን
አይነ ኮሎ ሽንጠ ሎጋ የወለዱ እንደሆን
መልካም ፀባይ ያላት የወለዱ እንደሆን
እውቀት የምትሻ የወለዱ እንደሆን
ታመጣለች አማች ብረት መዝጊያ የሚሆን
ታመጣለች አማች ብረት መዝጊያ የሚሆን
ማማዬ ማማዬ ኸረ ነይ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ ኸረ ነይ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ ኸረ ነይ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ ኸረ ነይ ማማዬ
ማማዬ ማማዬ ሸጋ ልጅ ማማዬ



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Mikeyas Cherinet
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link