Meknatsh Temechegne

እንደተዳፈነ
እንዳልጠፋ እሳቱ
ዛሬ ገብቶኛል ያንቺ መንገድ
እየቀኑ መውደድ
ምልክትሽ ሲሆን
ፍቅርን ማሳያሽን
ያኔ እንዳላልኩሽ ተይ ሰለቸኝ
መቅናትሽ ተመቸኝ

የት ገባህ የት ወጣህ
ሲል አፍሽ ላመሉ
ምን በላህ ምን ጠጣህ
የምትዪኝ ሁሉ

ለካስ ፍቅር ነው
ቅናት ሚመስለው
ለካስ መውደድ ነው
ክፋት የሌለው

ቅናት ጉትጎታሽን
ሳልሰማ ካደርኩኝ
ይመስለኝ ጀምሯል
ያነስኩ የጎደልኩኝ

ለካስ ፍቅር ነው
ቅናት ሚመስለው
ለካስ መውደድ ነው
ክፋት የሌለው

እንደተዳፈነ
እንዳልጠፋ እሳቱ
ዛሬ ገብቶኛል ያንቺ መንገድ
እየቀኑ መውደድ
ምልክትሽ ሲሆን
ፍቅርን ማሳያሽን
ያኔ እንዳላልኩሽ ተይ ሰለቸኝ
መቅናትሽ ተመቸኝ

ለክፉም ለደጉም
ለዋሾም ላባዩም
ፍቺው ይለያያል
ልክ እንደ አተያዩ

ለካስ ፍቅር ነው
ቅናት ሚመስለው
ለካስ መውደድ ነው
ክፋት የሌለው

ሰው አይቀናምና
ሆን ብሎ ፈልጎ
ወደሽ መቅናትሽን
አየሁት በበጎ

ለካስ ፍቅር ነው
ቅናት ሚመስለው
ለካስ መውደድ ነው
ክፋት የሌለው(3)



Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Meselle Getahun
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link