Lyewa Lyew

ሃሰት ከሌለበት ከፍቅር መኖርያ
ከመውደድ ማረፍያ መዋያ ማደርያ
ከልብሽ ጓዳ ያለውን መውደድ
አውጪና እስቲ ልየው ፍቅርን በገሃድ

ሃሰት ከሌለበት ከፍቅር መኖርያ
ከመውደድ ማረፍያ መዋያ ማደርያ
ከልብሽ ጓዳ ያለውን መውደድ
አውጪና እስቲ ልየው ፍቅርን በገሃድ

ለኔ እንዳወጋሽኝ እንደቃልሽ ውሉ
ፍቅርሽ ተጋጊጦ እውነታን ተክኖ
መውደድሽን ልየው ፈክቶ እንደ አበባ
ፍቅርሽ ከልቤ ውስጥ ዘልቆ እንዲገባ
ፍቅርሽ ከልቤ ውስጥ ዘልቆ እንዲገባ

ልየው አልየው የልብሽን ጓዳ
ድፍርስርስ ስሜቴ በፍቅርሽም ይጽዳ
ልየው አልየው ስለኔ ያለሽን
የፍቅር የመውደድ ውስጣዊ ስሜትሽን

ልየዋ ልየው ልየዋ እስቲ ልየው
ወግስ በዓይን ይገባል ፍቅርም እንደዛው
ልየዋ ልየው ልየዋ እስቲ ልየው
ወግስ በዓይን ይገባል ፍቅርም እንደዛው

ሃሰት ከሌለበት ከፍቅር መኖርያ
ከመውደድ ማረፍያ መዋያ ማደርያ
ከልብሽ ጓዳ ያለውን መውደድ
አውጪና እስቲ ልየው ፍቅርን በገሀድ

ሃሰት ከሌለበት ከፍቅር መኖርያ
ከመውደድ ማረፍያ መዋያ ማደርያ
ከልብሽ ጓዳ ያለውን መውደድ
አውጪና እስቲ ልየው ፍቅርን በገሀድ

ጽድቅም የሚገኘው እምነት ሲሆን ምግባር
ብለሽም አሳይኝ ፍቅርሽን በተግባር
አንቺም የእምነትሽን ተይ እንድታገኚ
ባንቺ ረሃብ ሞቼ እንዳትኮነኚ
ባንቺ ረሃብ ሞቼ እንዳትኮነኚ

ልየው አልየው የልብሽን ጓዳ
ድፍርስርስ ስሜቴ በፍቅርሽም ይጽዳ
ልየው አልየው ስለኔ ያለሽን
የፍቅር የመውደድ ውስጣዊ ስሜትሽን

ልየዋ ልየው ልየዋ እስቲ ልየው
ወግስ በዓይን ይገባል ፍቅርም እንደዛው
ልየዋ ልየው ልየዋ እስቲ ልየው
ወግስ በዓይን ይገባል ፍቅርም እንደዛው
ልየዋ ልየው ልየዋ እስቲ ልየው
ወግስ በዓይን ይገባል ፍቅርም እንደዛው
ልየዋ ልየው ልየዋ እስቲ ልየው
ወግስ በዓይን ይገባል ፍቅርም እንደዛው



Credits
Writer(s): Elias Melka
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link