Sew

የደመቀው ጀንበር ይጠቁራል በክረምት
እድሜም በወቅት ያልቃል መውደድ በወረት
እውነተኛ አፍቃሪ ማህተቡ ለፅድቅ
ሲኖር አብሮ በልቶ ሲቸገሩ አይርቅ
የበደል አበባ ያበቃላት ለቅሶ
ፍቅር ነኝ ትላለች ደግሞ በርሷም ብሶ
ቢወሻሽ ነው እንጂ አንዱም ላይጎዳ
ምን አሸዋወደ አራዳ ላራዳ

መሰን ተቃርቦ ተይቅር ሎቦ

ሲርቋት ተከታይ ሲላመዷት ባዳ
አትዘልቅ ካንድ ቤት ሁለት ቢላ ለምዳ
አመሏ አይታወቅ ፍዝ ያገነናት
እሳት ሲሏ ውሃ ማር ሲላት እሬት
እንደሰማይ ጀንበር ሁሌ እየደመቀ
ተመልሶ አይወጣም እድሜም ከጠለቀ
ዘመን እያባራ ሁሎ አይኖር ስቆ
ውበትም ይመሻል ጊዜው ጠብቆ
ጀንበር ሲጠልቅ ሲሸሽ ሳቅ ሲተካው ለቅሶ
ያ ያማረው ወራት አይገኝ መልሶ
መወደዷን አውቃ መልኳ ስላማረ
እኮራለሁ ብላ ተረስታ ነበረ

አዝማች

መሄድ መሄድ ያለ ውሎ አዳሩ ጀጅ
እንኳንስ ለወዳጅ ለራሱም አይበጅ
ያንጀት ወዳጅ መስሎ ትልቅ ጉድጓድ ምስ
ንጉሥም ለብልሃት ያበላል ደግሶ
መስቀል ዘ ሰላጢ ከመፅሐፍ ጠቅሳ
እመነኝ አለችኝ ልትቀብረኝ ምሳ
ተምራ ተክና ላሳር ለኩነኔ
ደቁና ስትመጣ ቄስ ሆንኩባት እኔ

ጀንበር ሲጠልቅ ሲሸሽ ሳቅ ሲተካው ለቅሶ
ያ ያማረው ወራት አይገኝ መልሶ
መወደዷን አውቃ መልኳ ስላማረ
እኮራለሁ ብላ ተረስታ ነበረ

እንደሰማይ ጀንበር ሁሌ እየደመቀ
ተመልሶ አይወጣም እድሜም ከጠለቀ
ዘመን እያባራ ሁሎ አይኖር ስቆ
ውበትም ይመሻል ወራትን ጠብቆ

መወሰንን ተቂርቦ ተይቅር ሎቦ



Credits
Writer(s): Teddy Afro
Lyrics powered by www.musixmatch.com

Link